ኦሮሚያ ባንክ በሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ያስገነባዉን ለቅይጥ አገልግሎት የሚዉል ባለ 11 ወለል ህንፃ አስመረቀ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ኦሮሚያ ባንክ በሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ ያስገነባዉን ለቅይጥ አገልግሎት የሚዉል ባለ 11 ወለል ህንፃ አስመረቀ።
ባንካችን በገላን ከተማ አስተዳደር በሚገኘው የልህቀት እና ኮንቬንሽን ማዕከሉ ወስጥ ያስገነባውን ባለ 11 ወለል የቅይጥ አገልግሎት ሕንፃ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የባንካችን ከፍተኛ ባለአክሲዮች፣ ባለድርሻ አካላት እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኦቦ ተፈሪ መኮንን፣ ''ባንካችን የህዝብ ባንክ መሆኑን ገና በማለዳው በገባው ቃልኪዳን መሠረት ከህዝብ ያገኘውን ቅቡልነቱን እንደ ቀዳማይ ዓላማ ይዞ 17 የስኬት ዓመታትን ተጉዟል። ሁሌም ከባንክ አገልግሎቶቹ ባሻገር ማህበራዊ ዕሴቶቹን በማጎልበት የህዝብን ጥቅም ባማከሉ ጉዳዮች ላይ መዋዕለንዋዩን እያዋለ ይገኛል'' ብለዋል።
ለማዕከሉ ግንባታ የሚሆን መሬት ከማቅረብ ጀምሮ ከባንኩ ያልተለዩት በኦሮሚያ ክልለል ም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ክቡር ዶ/ር ተሾመ አዱኛ፣ የገላን ከተማ አስተዳደር፣የአንዶዴ ወረዳ አስተዳደር፣ እንዲሁም በህንጻዉ ግንባታ ላይ የተሳተፉትን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ኦቦ ተፈሪ አመስግነዋል።
የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አሰፋ ስሜ በበኩላቸው ኦሮሚያ ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን የሚቀርፉ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እየሰራ እንደሚገኝ እና ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ሼህ ሐጅ እብራሂም ቱፋ ኦሮሚያ ባንክ ከሁሉም ባንኮች ቀድሞ የሙስሊሙን ማህበረሰብ የባንክ ተጠቃሚ ያደረገ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንዳስተዋወቀ ሁሉ በልማት ስራዎችም በግንባር ቀደምነት የሚሳተፍ የህዝብ ባንክ ነዉ ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል ም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ ክቡር ዶ/ር ተሾመ አዱኛ በበኩላቸው ለገላን ከተማ ልዩ ድምቀት የሚሰጠዉ ይህ ህንፃ የተለያዩ የንግድ ስራ ለተሰማሩ የከተማዉ ነዋሪዎች መልካም ዕድል ከመምጣቱም በላይ መንግስት ስማርት ሲቲን ለመገንባት እያደረገ ላለዉ ርብርብ ተጨማሪ ዉበት የሚያላብስ መሆኑን ተናግረዋል።
#OromiaBank