ከ300 በላይ የሽብር ተከሳሾች የቀረበላቸው የይቅርታ ሰነድ ምን ይዟል ?
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ከ300 በላይ የሽብር ተከሳሾች የቀረበላቸው የይቅርታ ሰነድ ምን ይዟል ?
ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር የተከሰሱ ከ300 በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ ከእስር እንዲለቀቁ ሂደት መጀመሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
የይቅርታ ሂደቱ እንዴት ጀመረ ?
እንደ ዘገባው ከሦስት ዓመት እና ከዚያ በላይ በእስር ላይ የሚገኙት ተከሳሾች የይቅርታ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚጠይቀው ሰነድ የደረሳቸው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አማካኝነት ነው።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል በተከሳሾቹና በመንግሥት መካከል የማሸማገል ሥራ ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ፣ ተከሳሾቹ ይቅርታ የሚጠይቁበትና የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን የያዘ ሰነድ ለየግላቸው ደርሷቸዋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ከተከሳሾቹ ጋር በፊትም ተገናኝተው ነበር።
በታኅሣሥ ወር ከኢሰመኮ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ወደ ፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ቂሊንጦ የጊዜ ቀጠሮ ማረፊያ ማዕከል ሄደው ተከሳሾቹን ጎብኝተው ነበር።
በዚያም ስለሰብዓዊ መብት አያያዝና ሌሎች ጉዳዮች ከተከሳሾቹ ጋር ተወያይተዋል።
ከዚህ ጉብኝት ከስድስት ወራት በኋላ ነው ኮሚሽነሩ በድጋሚ ከተከሳሾቹ ጋር በመገናኘት የማደራደር ሥራ የጀመሩት።
ሰነዱ ተከሳሾች ምን እንዲያምኑ ይጠይቃል ?
ሰነዱ ተከሳሾቹ በየክስ መዝገባቸው የቀረበባቸውን ወንጀል እንደፈጸሙ አምነው ኃላፊነት እንዲወስዱ ይጠይቃል።
ሰነዱ በተለይ ፦
- በአማራ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ኃላፊነት እንዲወስዱ፤
- በግጭቱ ለሞቱና ለቆሰሉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ኃላፊነት እንደሚወስዱ እንዲያምኑ፤
- በቢሊዮኖች የሚገመተውን የንብረት ውድመት እንደፈጸሙ እንዲያምኑ፤
- በየክስ መዝገባቸው የተጠቀሱትን የሽብር ወንጀሎች እንደፈጸሙ እንዲቀበሉ፤
- ወደፊት በተመሳሳይ ድርጊት እንደማይሳተፉ ቃል እንዲገቡ፤
ቃላቸውን ካፈረሱ መንግሥት አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድባቸው እንደሚስማሙ እንዲገልጹ ይጠይቃል።
ከፖለቲካዊ አቋማቸው ጋር የተያያዙ ምን ጉዳዮች ተካተዋል ?
ሰነዱ ላይ "አንፈርምም" ካሉ ተከሳሾች በተገኘው ምላሽ ከወንጀል ክሶች በተጨማሪ ከፖለቲካዊ አቋሞቻቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በሰነዱ ላይ ሰፍሯል።
በተለይ፦
1. "አገሪቱ በአማራ ትውፊቶችና እሳቤ መመራት አለባት" የሚል አቋም ማራመዳቸው ወንጀል መሆኑን እንዲያምኑ፤
2. "ያለአግባብ የተወሰዱ የአማራ ርስቶች መመለስ አለባቸው" የሚል አቋም መያዛቸውም ወንጀል መሆኑን እንዲቀበሉ፤
3. በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ "ጽንፈኛ ኃይሎች" ተብለው የተጠቀሱ ታጣቂዎችን እንዲያወግዙ ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል።
ስንቶቹ ፈረሙ ? ስንቶቹ አልፈረሙም ?
በተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙት ከ300 በላይ ተከሳሾች ሰነዱን እንዲፈርሙ ቀርቦላቸዋል።
አብዛኛዎቹ ፈርመዋል፤ ነገር ግን 30 የሚያህሉ ተከሳሾች ቅድመ ሁኔታዎቹን በመቃወም እንዳልፈረሙ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቅርብ ቤተሰባቸው ባገኘው መረጃ " አንፈርምም " ያሉት 30 ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው።
1. አቶ ዮሐንስ ቧያለው
2. ዶ/ር ወንድወሰን አሰፉ
3. ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው
4. ዶ/ር መሰረት ቀለምወርቅ
5. ዶ/ር ቴውድሮስ ሀ/ማርያም
6. ጋዜጠኛ ጐበዜ ሲሳይ
7. ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው
8. ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱ
9. ጋዜጠኛ መስከረም አበራ
10. ጋዜጠኛ ገነት አስማማው
11. አቶ አለልኝ ምህረቱ
12. አቶ መንበር አለሙ
13. አቶ ማይክ መላክ
14. አቶ እስክንድር ሽፈራው
15. አቶ ደሳለኝ እጅጉ
16. አቶ አሳምነው ታደሰ
17. አቶ መሰለ ቸሩ
18. አቶ እሱባለው በለጠ
19. ዶ/ር ዘሪሁን በሀራው
20. ኢ/ር ፍርዱ ተፈራ
21. ወ/ሪት ሀሊማ መሐመድ
22. ወ/ሪት ህይወት አላምረው
23. አቶ ጫኔ ዘገየ
24. አቶ ሲሳይ መልካሙ
25. አቶ ማረው ስለሺ
26. አቶ ታደሰ ወልድነው
27. አቶ ያሬድ ግርማ
28. አቶ ሰለሞን ተፈራ
29. አቶ ሙሉቀን ተስፉ
30. አቶ በላይ ሲሳይ
እነዚህ 30 ተከሳሾች ፥ በፍርድ ቤት የተከሰሱበትን ወንጀል እየተከራከሩ እያለ "ወንጀለኛ ነን" ብለው መፈረም እንደማይችሉ ገልጸዋል።
" ወንጀለኛ ነን ብለን አንፈርምም፤ ይህ በሕግም፣ በሞራልም፣ በፖለቲካም ተቀባይነት የለውም " የሚል አቋም ይዘዋል።
" የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎችም ሕጋዊ ናቸው ብለን እናምናለን " ሲሉም አክለዋል።
30ዎቹ ተከሳሾቹ ምን ይፈልጋሉ ?
እነዚህ ተከሳሾች ከሦስት ዓመት በላይ ያለ ፍርድ በእስር መቆየታቸውን በመጥቀስ፣ ጉዳዩ በምህረት እንዲፈታ ይፈልጋሉ።
ቤተሰቦቻቸው ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን የሚገልፁት ተከሳሾች፣ መንግሥት " ክሱን አቋርጦ በፖለቲካዊ መንገድ በምህረት ይፍታን " የሚል አቋም አላቸው።
የሕግ ጥያቄውስ ?
ለቢቢሲ ቃላቸውን የሰጡ የሕግ ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ጥላሁን፣ በኢትዮጵያ የይቅርታ ሂደት ላይ የመጨረሻ የፍርድ ውሳኔ መኖሩ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 229 እና በይቅርታ አዋጅ 840/2006 አንቀጽ 15 መሠረት፣ የይቅርታ ጥያቄ በወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የመጨረሻ ቅጣት በተወሰነበት ሰው ላይ እንደሚቀርብ አቶ ኤርሚያስ አብራርተዋል።
በዚህ ጉዳይ ግን ተከሳሾቹ ገና ፍርድ ያላገኙ ሲሆን፣ ክሳቸውም በተለያየ የሕግ ሂደት ላይ ይገኛል።
ስለዚህ የቀረበው ሂደት ከመደበኛው የይቅርታ አሠራር ጋር እንዴት እንደሚጣጣም የሕግ ጥያቄ አስነስቷል።
ኢሰመኮ ምን አለ ?
ቢቢሲ ስለ ድርድሩ ኢሰመኮን ለማነጋገር ሞክሯል። የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ግን በጉዳዩ ላይ መረጃ እንደሌላቸው ተናግረዋል።
ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia