ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

"ዘመናዊነትን ለመቀበል ባህላቸውን መጣል አስፈላጊ አይደለም።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
"ዘመናዊነትን ለመቀበል ባህላቸውን መጣል አስፈላጊ አይደለም።
"ዘመናዊነትን ለመቀበል ባህላቸውን መጣል አስፈላጊ አይደለም። እኛ አሁን የተዛባ አመለካከት አለን፤ ዘመናዊ ለመሆን ባህልን እና ማንነትን አሽቀንጥሮ መጣል አያስፈልግም"- የታሪክ መምህር አቶ በላይ ስጦታው

የቡሄ በዓል ሲደርስ ልጆች የሚጫወቱት "ሆያ ሆዬ"፣ የሚያጮሁት ጅራፍ እና የሚታደሉት "ሙልሙል ዳቦ" ሃይማኖታዊና ባህላዊ ሚስጢሩ ምንድን ነው? አሁን ባለው የዲጂታል ዘመንስ ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ ምን መደረግ አለበት?

​ቲክቫህ ኢትዮጵያ በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ የታሪክ መምህሩን አቶ በላይ ስጦታውን አናግሯል።

የደብረ ታቦር (ቡሄ) በዓልን በሃይማኖታዊና ባህላዊ ሁነቶች ስናከብር ይዘቱ እንዳይሸረሸር ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ የታሪክ መምህሩ አቶ በላይ ስጦታው አሳስበዋል።

"በዓሉ በመንግስት ህግ የተደነገገ ሳይሆን ህዝቡን በነፃነትና በፍቅር አስተሳስሮ የቆየ ድንቅ የጋራ እሴት መሆኑን" ተናግረዋል።

አክለውም፣ በየዓመቱ የሚከናወኑት የሙልሙል ዳቦ፣ የጅራፍ እና የሆያ ሆዬ ጭፈራ ባህሎች በሙሉ በደብረ ታቦር ተራራ ከተፈጸሙ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ክስተቶች ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው አብራርተዋል።

የታሪክ መምህሩ በዝርዝር ምን አሉ?

ያንብቡ - https://www.facebook.com/share/p/14vQMGeKh7D/

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች