" ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በርካታ ሞተር ሣይክሎች ተይዘዋል በሞተር እየተንቀሳቀሱ ያሉት ፖሊሶችና ትራፊኮች ብቻ ናቸው ፤ ግን እነሱም አብዛኞቹ መንጃ ፈቃድ የላቸውም " - ነዋሪዎች
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በርካታ ሞተር ሣይክሎች ተይዘዋል በሞተር እየተንቀሳቀሱ ያሉት ፖሊሶችና ትራፊኮች ብቻ ናቸው ፤ ግን እነሱም አብዛኞቹ መንጃ ፈቃድ የላቸውም " - ነዋሪዎች
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፣ የከተማው ፖሊስ እና ትራንስፖርት መምሪያ ዛሬ ከማለዳ አንስቶ በድንገት ከመንጃ ፈቃድና ሄልሜት ጋር በተያያዘ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሞተር ሳይክሎችን እያዋከቡ በማስቆም መያዛቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
" ሞተር ሳይክል በድንገት በፖሊሶች ተወስዶብኛል " ያለን አንድ ነዋሪ " መረጃና ግንዛቤ ሳይሰጠን በድንገት ብቻ በማዋከብ ሞተር እያስቆሙ አሽከርካሪ ' መንጃ ፈቃድና ሄሊሜት አላሟላህም/ሽም ሞተርህን/ሽን ለቀህ ሂድ ' እያሉ ተቀበሉን " ሲሉ አስረድተዋል።
ሌሎች ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ " ወከባው ሌላ ነገር የተፈጠረ ነው የሚመስለው፤ ብዙ ሞተር ሳይክሎች ተይዘዋል፣ መፍትሄውን ስንጠይቅ 'ቢሮ ሄዳችሁ አነጋግሩ' ከሚል ምላሽ ውጪ በአግባቡ የሚያናግረን አላገኘንም " ብለዋል።
በርካታ የጤና ባለሙያዎች፣ መምህራን አስቸኳይ ስራ ያላቸው ግለሰቦች ጭምር መንገድ ላይ ስንገላቱ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ሌሎች ነዋሪዎች " ሕዝብ አንድ መንጃ ፈቃድ ያለን ሰዎች ከዚህ ቀደም አውቶሞቢል እና ሞተር ሳይክል ለማሽከርከር አንከለከልም ነበር ዛሬ ግን 'የሞተር ሳይክል ብቻ አምጡ' ተብለን ሞተር ሳይክል ተወስዶብናል " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
" በከተማዋ ዛሬ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሞተሮች የፖሊስና የትራፊኮች ናቸው " የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " አብዛኛው ፖሊስና አመራርም ቢሆን የሞተር መንጃ ፈቃድ የለውም " ሲሉ አክለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በሀዋሳ ከተማ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች የሞተር ሳይክሎች ቁጥር ከወትሮው በጣም መቀነሱን አስተውሏል።
ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም ምላሻቸውን ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia