ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ' የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ተዘግቷል ' ፣  ' ዜጎች እየተሰማሩ አይደለም '  ወዘተ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ ናቸው " - ሚኒስቴሩ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ' የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ተዘግቷል ' ፣  ' ዜጎች እየተሰማሩ አይደለም '  ወዘተ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ ናቸው " - ሚኒስቴሩ
" ' የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ተዘግቷል ' ፣  ' ዜጎች እየተሰማሩ አይደለም '  ወዘተ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ ናቸው " - ሚኒስቴሩ

በኢትዮጵያና ሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምምነት ዙሪያ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ሰጠ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር " በኢትዮጵያና በሳዑዲ አረቢያ መካከል ስላለው የሥራ ስምምነት እና የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ሂደት ዙሪያ የተለያዩ የተሳሳቱና መሠረተ ቢስ መረጃዎች ሲሰራጩ ተመልክተናል " ሲል ገልጿል።

" ሳዑዲ አረቢያ ለኢትዮጵያውያን የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ዋና መዳረሻ ከሆኑ አገራት አንዷ ናት " ያለው ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ ቁጥጥር የሚደረግበት የውጭ አገር የሥራ ስምሪት ማዕቀፍ ውስጥ ቁልፍ አጋር ሆና መቀጠሏን ገልጿል።

በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ስምሪት ውስጥ የሚሠሩትን ጨምሮ፣ በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ምኅዳር ውስጥ ፈቃድ ያላቸው የቅጥር ኤጀንሲዎች የዚህ ሂደት የማይነጠል አካል ሆነው መቀጠላቸውን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በሥራ ስምሪት ሂደት ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶችንና ክፍተቶችን ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በማጣራት የማስተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ መሆኑንም ገልጿል።

ነገር ግን፣ " የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ ተዘግቷል " ፣ " ዜጎች እየተሰማሩ አይደለም " ወዘተ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሠረት የለሽ ናቸው ያለው ሚኒስቴሩ፥ " ይልቁንም ሕጋዊ የሥራ ስምሪት ሂደቱ በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓቱ እየተቀላጠፈ የቀጠለ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን " ብሏል።

ዜጎች እነዚህን በመሰሉ ከእውነት የራቁ መረጃዎች እንዳይደናገሩ እያሳሰበ፣ መሠረት የለሽና አሳሳች መረጃዎችን በሚያሰራጩ አካላት ላይ ማጣራት በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች