" የባህር በር እጦት በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ እንድትከፍል እያደረገ ነው " - አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር)
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" የባህር በር እጦት በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ እንድትከፍል እያደረገ ነው " - አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር)
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ የሕልውና ጉዳይ ነው ተባለ።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ወሳኝ እና የሕልውና ጉዳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) ገለጹ።
የባህር በር አለመኖሩ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ ጨምሮ በቢሊዮኖች የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ ወጪ እንዲወጣ እያስደረገ እና የሸቀጦች የወጪና ገቢ እንቅስቃሴ እንዲዘገይ በማድረግ በኢኮኖሚው ላይ ጉልህ ተፅዕኖ እና ጉዳት እያደረሰ ነው ብለዋል።
ይህ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት የሀገርን ተፈጥሯዊ ፣ መልክዓ ምድራዊ ፣ ስትራቴጂካዊና ሕጋዊ የባህር በር ባለቤትነት ለማስመለስ ያነሱትን ጥያቄ ምክንያታዊነት ያጎላዋል ሲሉ ለኢዜአ ገልጸዋል።
መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia