ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የታጠፈው ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የታጠፈው ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን
የታጠፈው ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

በድጋሚ በተሻሻለውና የከተማዋ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ሥልጣና ተግባሩ እንዲታጠፍ የተወሰነው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ገና እንዳልደረሰው ገለጸ።

• የባለሥልጣኑ አጠቃላይ የሰራተኞቹ ብዛት ከ 1 ሺ 200 በላይ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ትላንት ያሻሻለ ሲሆን፣ የተሻሻላው አዋጅ አንዳንድ ተቋማት ላይ የመታጠፍ፣ የመክፈልና የማዋሃድ ውሳኔዎች አሳልፏል።

​ከእነዚህም ውሳኔዎች መካከል ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 84/2016 መሰረት ከአገልግሎት ሰጪ «ኤጀንሲ» ወደ «ባለስልጣን» ከፍ ብሎ ተቋቁሞ የነበረው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን፣ ስልጣንና ተግባሩ ለሌሎች መስሪያ ቤቶች ተከፋፍሎ እንዲሰጥ ተደርጎ እንዲታጠፍ መወሰኑ ይገኝበታል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ​ጉዳዩን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊ በሰጡት ምላሽ "ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ገና አልደረሰንም፤ እንደደረሰን ይፋ የምናደርግ ይሆናል" ብለዋል።

በመስሪያ ቤቱ ስራቸውን ሲያከናውኑ የነበሩ ሰራተኞች ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው ሌላኛው የተቋሙ የበላይ አመራር ደግሞ " ውሳኔውን የሰማሁት ምክር ቤት ላይ ሲነሳ ነው የሪፎርም ተቋማት ጥናት አዳማ ላይ እየተደረገ ይገኛል ጥናቱ ሰራተኞቹ ወዴት እንደሚጠቃለሉ አያሳይም ቀጣዩን ሂደት በተመለከተ መረጃው የለኝም " ብለውናል።

በአሁኑ ሰአት በተቋሙ ስራቸውን እያከናወኑ የሚገኙ ሰራተኞች ቁጥር ከ1ሺ 200 በላይ መሆኑንም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተቋሙ ማረጋገጥ ችሏል።

​ውሳኔው የተላለፈበት ምክንያትና የስልጣን ክፍፍሉ ​በከተማዋ የትራፊክ ህግ ማስከበር ስራ ላይ የተለያዩ አካላት በተበታተነ መልኩ መሰማራታቸው ያስከተለውን የመልካም አስተዳደር ችግርና የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት ሲባል የተላለፈ ውሳኔ መሆኑ በምክር ቤቱ ተብራርቷል።

​በዚህም መሰረት የታጠፈው ባለስልጣን ስልጣንና ኃላፊነቶች ለከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ፣ የመንገዶች ባለስልጣን እና ​አዲስ የሚደራጀው የትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል መተላላለፉን ይፋ ተደርጓል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች