" የግጭቱ መንስኤ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሳያነጋግሩ ለኢንቨስትመንት ቦታ በመሰጠቱ ነው " - የገረሴ አከባቢ ነዋሪዎች
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" የግጭቱ መንስኤ የአካባቢውን ነዋሪዎች ሳያነጋግሩ ለኢንቨስትመንት ቦታ በመሰጠቱ ነው " - የገረሴ አከባቢ ነዋሪዎች
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻሌ ቀበሌ ከኢንቨስትመንት ቦታ ማስፋፊያ ጋር በተያያዘ በተከሰተ ግጭት የሰዎች ሕይወት ማለፉን የአከባቢው ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።
አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያለፈለገ የአከባቢው ነዋሪ ፥ ላለፉት አምስትና ስድስት ዓመታት በአከባቢው ሲንቀሳቀስ ለቆየ አንድ የኢንቨስትመንት ድርጅት አዲስ የቦታ ማስፋፊያ ጥያቄ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ሳያማክሩ በመስጠታቸው የተፈጠረ አለመግባባት እና ግጭት ለ21 ሰዎች የሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል ሲል ተናግሯል።
ሌላኛው የገረሴ ነዋሪም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል የሟቾቹን ቁጥር ወደ 22 አድርሶ " ሕይወታቸው ካለፉት ሰዎች መካከል 12ቱ የኢንቨስትመንት ተቋሙ ሰራተኞች ናቸው 10ሩ ደግሞ የፖሊስ አባላትና የፀጥታ አካላት ናቸው " ብለዋል።
ዛሬም ድረስ ያልተገኙ የፀጥታ አካላት አስክሬኖች ስለመኖራቸው የገለፁት ነዋሪዎቹ አሁን ላይ በአከባቢው አንፃራዊ ሰላም መስፈኑን ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ጉዳዩ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ለማግኘት ባደረገው ሙከራ የዞኑ ፖሊስ መረጃ እንዲሰጥ ቢያመቻችም የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ተጨማሪ ጉዳዮችን በማጥራት መረጃ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።
የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ፣ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሻለ ቀበሌ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለማረጋጋት ወደ ሥፍራው በተንቀሳቀሱ የፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት ላይ "ሕገ ወጥ ቡድኖች" በከፈቱት ተኩስ የፀጥታ መዋቅር አባላት ሕይወት ማለፉን አረጋግጧል።
መምሪያው " መተክያ የማይገኝለት ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች በሙሉ የተሰማንን ሀዘን እንገልጻለን እኚህ ጀግኖች በአገልግሎታቸው ያበረከቱት አስተዋፅኦና የሙያ ትጋት ሁሌም በክብር ይታሰባል " ብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia