የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር አዋለ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

የፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖልና ከማላዊ ፖሊስ ጋር በመተባበር አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በቁጥጥር ሥር አዋለ።
ፖሊስ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪው ከሀድያና ከንባታ ዞኖች ወጣቶችን ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሳቸው በማታለል ከእያንዳንዱ ተጓዥ ከ600 ሺህ እስከ 800 ሺህ ብር ይቀበል ነበር።
ተጎጂዎችን በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ በማሻገር፣ በጫካ ውስጥ በድብቅ ያቆያቸው፣ በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ ብቻ ትንሽ ሩዝና ቁራጭ ዳቦ በመስጠት ለከፍተኛ ረሃብና ጥም ይዳርጋቸው ነበር። በተጨማሪም በሞተርና በእግር ሴሎ በረሃን እንዲያቋርጡ ያስገድዳቸው ነበር።
ናይሮቢ ከደረሱ በኋላም በአንድ ክፍል ውስጥ አጉሮ ከቤተሰቦቻቸው ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስልኩ ያስገድዳቸው ነበር። ገንዘብ ማስላክ ያልቻሉትን በዱላ ይደበድባቸው፣ "እዚሁ ትሞታላችሁ" በማለት ያስፈራራቸው እንዲሁም በኤሌክትሪክ ንዝረት ያሰቃያቸው እንደነበር ፖሊስ ገልጿል።
ከዚያም ተጓዦችን በዕቃ መጫኛ ኮንቴነሮችና በተሸፈኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ታንዛኒያ በማጓጓዝ በጫካ ውስጥ ጥሎ ይተዋቸው እንደነበር ተገልጿል።
በዚህ ምክንያትም ብዙ ተጎጂዎች ደቡብ አፍሪካ ሳይደርሱ በየመንገዱ በፖሊስ ተይዘው እስር ቤት መግባታቸውንና በኋላም ገንዘብ ከፍለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን ፖሊስ አመልክቷል።
ተጠርጣሪው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገ ክትትል በማላዊ ተይዞ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ተላልፎ ተሰጥቷል።
ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia