" ይቅርታ ተጠያይቆ አዲስ የሕይወት ጉዞ መጀመር ይገባል " - የታሪክ መምህር በላይ ስጦታው
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ይቅርታ ተጠያይቆ አዲስ የሕይወት ጉዞ መጀመር ይገባል " - የታሪክ መምህር በላይ ስጦታው
ጳጉሜን ወር የአሮጌው ዓመት መጨረሻ ብቻ ሳትሆን፣ ኢትዮጵያውያን በይቅርታ፣ በፍቅርና በሰላም ወደ አዲሱ ዓመት የሚሸጋገሩበት ልዩ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ወቅት መሆኗን የታሪክ መምህር በላይ ስጦታው ገለጹ።
መምህሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ ጳጉሜን የሚለው ቃል ከግሪክ የመጣ ሲሆን «ጭማሪ» ማለት እንደሆነ ጠቅሰው፣ ወሩ ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዓመት የሚያሻግር ድልድይ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህ ወቅት ሰዎች ያለፈውን በደልና ቂም በመተው፣ የበደሉት ይቅርታ በመጠየቅ፣ የተበደሉት ደግሞ ይቅር በማለት በአዲስ መንፈስ ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በባህላዊ አሠራርም ይቅርታ በቃል ብቻ ሳይሆን በድርጊት ይገለጽ እንደነበር ያስታወሱት መምህሩ፣ ሽማግሌዎች በማስታረቅ የተበደለና የበደለ ወገን እንዲታረቁ ያደርጉ እንደነበር ገልጸዋል።
በተጨማሪም የጳጉሜን ባህላዊ እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊተላለፉ እንደሚገባ፣ ቤተሰብ ልጆችን በባህልና ታሪክ ማሳደግ እንዳለበት እና ባህላዊ እሴቶችም በትምህርት ካሪኩለም ሊካተቱ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የአዲስ ዓመት በዓል በወጣቶች ዘንድ ከባህላዊ እሴቱ እየራቀ መምጣቱንም በመጥቀስ፣ ቀድሞ ወጣቶች በቡድን በመዞር ዳቦንና ሌሎች ስጦታዎችን በመሰብሰብ አብረው ይመገቡና ፍቅርን ያጠናክሩ እንደነበር አስታውሰዋል።
" ጳጉሜን ሰው ሸክሙን የሚያራግፍበት፣ ከወገኑ ጋር የሚታረቅበትና በፍቅርና በይቅርታ አዲስ ጉዞ የሚጀምርበት ወር ናት " ያሉት መምህር በላይ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከወገኑ ጋር ይቅርታ ተጠያይቆ በአዲስ መንፈስ የሕይወት ጉዞውን እንዲጀምር ጥሪ አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia