" ግለሰቡ ' ተሰድቤያለሁ ሰው እገድላለሁ ፤ እኔም እራሴን አጠፋለሁ ' በሚል ' ቤተሰቦቼ የሚያለቅሱበትን የሀዘን መግለጫ ባነር ነው ያሰራሁት ' ነው ያለን " - የሰሜን ቤንች ፖሊስ አ…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ግለሰቡ ' ተሰድቤያለሁ ሰው እገድላለሁ ፤ እኔም እራሴን አጠፋለሁ ' በሚል ' ቤተሰቦቼ የሚያለቅሱበትን የሀዘን መግለጫ ባነር ነው ያሰራሁት ' ነው ያለን " - የሰሜን ቤንች ፖሊስ አዛዥ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሼኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሚዳ በተባለ አካባቢ የራሱን " ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ " የሚል የሐዘን መግለጫ ባነር በማሰራት፣ የተቀየመውን ሰው ገድሎ ራሱን ለማጥፋት ሲዘጋጅ የነበረ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ማዋሉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሺካ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ኢንስፔክተር ዘለቀ እንደገለፁት ድርጊቱን የፈጸመው አቶ ማሌች ሚቲኩ ገተራሻ የተባለ የ31 ዓመት አባወራ እና የሁለት ልጆች አባት ነው።
አቶ ማልች ከተጣላው አካል ጋር በነበረው አለመግባባት ግለሰቡ " ሟርተኛ " ሲል ሰድቦኛል በሚል በትናንትናው ዕለት መስከረም 12/2019 ዓ/ም በቂም በቀል ተነሳስቶ ግለሰቡን ለመግደልና እራሱንም ለማጥፋት አቅዶ ለዚሁ እቅዱ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ የራሱን የሐዘን መግለጫ ባነር በቅድሚያ አሳትሞ በማምጣት በዕለቱ መጠጥ እየጠጣና በማስፈራሪያዎች ሲፎክር ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዙን ገልፀዋል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ " ባነሩን ያዘጋጀሁት ቤተሰቦቼ እኔን እያሰቡ እንዲያለቅሱበት ነው " በሚል ለፖሊስ ቃሉን መስጠቱን ያነሱት የፖሊስ አዛዡ ድርጊቱ በአካባቢው አዲስና ያልተለመደ በመሆኑ ለህብረተሰቡ ግንዛቤና ማስጠንቀቂያ እንዲሆን በሚዲያ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኝ ሲሆን ጉዳዩ በሕግ አሰራር መሠረት የሚኖረውን ቀጣይ አካሄድ ከሚመለከታቸው የሕግ አካላት ጋር እየተመረመረ ይገኛል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia