ህይወቱ አልፏል የተባለው ተጨዋች ተነሳ !

ህይወቱ አልፏል የተባለው ተጨዋች ተነሳ !
በናይጄሪያ ሻምፒዮን ሺፕ የሚጫወተው ተጨዋች ቺኖዱ ኦዞር ህይወቱ አልፏል በሚል ሊቀበር ሲል መነሳቱ ተሰምቷል።
ተጫዋቹ በጨዋታ ላይ ራሱን ስቶ የነበረ ሲሆን የህክምና ባለሙያዎች ህይወቱ እንዳለፈ አሳውቀው ነበር።
የቡድኑ አባላትም የቡድን አጋራቸው ህይወት በማለፉ ሀዘን ተቀምጠው እንደነበር ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ተጨዋቹ ወደ አስከሬን ክፍል ውስጥ ከተወሰደ ጥቂት ጊዜ በኋላ እንቅስቃሴ ማሳየቱ ተነግሯል።
ተጨዋቹ በህይወት እንዳለ እና በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ተዘዋውሮ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን ክለቡ አሳውቋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe