"ለሲዳማ ቡና እሮጣለሁ" የደጋፊዎች ሩጫ ይፋ ሆነ

"ለሲዳማ ቡና እሮጣለሁ" የደጋፊዎች ሩጫ ይፋ ሆነ
ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ከዋናው የስፖርት አልባሳት ብራንድ እና BT Creative Event ጋር በመተባበር በሀዋሳ የሚያዘጋጀውን "ለሲዳማ ቡና እሮጣለሁ" የደጋፊዎች ሩጫ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የክለቡ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ከነአን በለጠ፣ ሩጫው የደጋፊዎችን አንድነት በማጠናከር ለክለቡ የፋይናንስ አቅምና ለአፍሪካ ውድድር ዝግጅት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው መላውን ደጋፊ እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
የደጋፊዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አብይ የናካ በበኩላቸው፣ ሩጫው ለክለቡ ያለውን ፍቅርና አንድነት የሚያሳይ መድረክ መሆኑን ገልጸው ደጋፊዎች ቲሸርቱን በመግዛት በሩጫው እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።
የዋናው የስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ማናጀር አቶ ዮሴፍ ሹምዬ፣ ለሩጫው የተዘጋጁት ቲሸርቶች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውና የክለቡን ማንነት የሚያንጸባርቁ መሆናቸውን ገልጸው፣ ዋናው የስፖርት አልባሳት ለዝግጅቱ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
የሩጫው ቲሸርቶች ከእሮብ ጀምሮ በሲዳማ ቡና የትጥቅ መሸጫ ሱቅ እና በደጋፊዎች ማህበር ቢሮ በ700 ብር ለሽያጭ ይቀርባሉ።
ይሄ ነው ዋናው!