ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ሊቨርፑል የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ሊቨርፑል የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው !
ሊቨርፑል የዝውውር ጥያቄ ሊያቀርብ ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ብራድሌይ ባርኮላን ለማስፈረም የመክፈቻ የዝውውር ሂሳብ ለማቅረብ ማዘጋጀቱ ተነግሯል።

ሊቨርፑል ብራድሌይ ባርኮላን የሞሀመድ ሳላህ ተተኪ ለማድረግ የመጀመሪያ ኢላማቸው አድርገዋል።

በፒኤስጂ የሁለት አመት ኮንትራት ያለው ባርኮላ ሊቨርፑልን የመቀላቀል ፍላጎት አለው።

ፒኤስጂ ለተጨዋቹ 1️⃣4️⃣5️⃣ ሚልዮን ፓውንድ እንደሚፈልግ ቢያሳውቅም ሊቨርፑል ያን ያህል ገንዘብ እንደማይከፍሉ ተነግሯል።

ሊቨርፑል ተጫዋቹን እስከ 1️⃣0️⃣0️⃣ ሚልዮን ፓውንድ ባለው ለማስፈረም ጥረት እንደሚያደርጉ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች