ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ማንችስተር ሲቲ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ማንችስተር ሲቲ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !
ማንችስተር ሲቲ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

ማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተሰላፊው ጄርሚ ዶኩን ውል ለተጨማሪ አመታት አራዝመዋል።

የ 24ዓመቱ ተጨዋች ጄርሚ ዶኩ በማንችስተር ሲቲ እስከ 2031 የሚያቆየውን የአምስት አመት ውል ፈርሟል።

ዶኩ ከፊርማው በኋላ “ በጣም ተደስቻለሁ በእኔ እምነት ስላደረባቸው በጣም ደስተኛ ነኝ “ ሲል ገልጿል።

አክሎም " ሁሉንም ዋንጫዎች ማሸነፍ እፈልጋለሁ በድጋሜ ለእያንዳንዱ ዋንጫ መፎካከር እፈልጋለሁ "ብሏል።

ጄርሚ ዶኩ በዚህ ክረምት ውሉን ለረጅም ጊዜ ያራዘመ አራተኛው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ሆኗል።

ፊል ፎደን ፣ ጆስኮ ግቫርዲዮል እና አብዱኮድር ኩሳኖቭ ውላቸውን ለረጅም ጊዜ ማራዘማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች