ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ማንችስተር ዩናይትድ ምን አይነት ጨዋታ አሳለፈ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ማንችስተር ዩናይትድ ምን አይነት ጨዋታ አሳለፈ ?
ማንችስተር ዩናይትድ ምን አይነት ጨዋታ አሳለፈ ?

የአሰልጣኝ ማይክል ካሪኩ ማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ በማድረግ ጥሩ ውጤት ይዞ ወጥቷል።

በተለይም በማጥቃቱ ረገድ ማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ ነገሮችን ያሳየበት ጨዋታ ነበር ።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ዳግም አስደናቂ አቋሙን ሲያሳይ ኮቢ ማይኖ አማካይ ክፍሉ ላይ ጥሩ ነገሮችን ሲሰራ ተስተውሏል።

ቡድኑ አሁንም የኋላ መስመሩን ክፍተት ማሻሻል ቢጠበቅበትም የውድድር አመቱን የመጀመሪያ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።

ብሩኖ ፈርናንዴ በማንችስተር ዩናይትድ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ እኩል ሶስት ሀትሪኮችን መስራት ችሏል።

ፈርናንዴዝ የሰራው ሀትሪክ በራሱ ጥሩ ጨዋታ እንዳደረገ ቢመሰክርም ሜዳ ላይ ያሳየው አቋም ግን ከዛም በላይ እንደነበር የሚያሳይ ነው።

ብሩኖ በጨዋታው ለምቤሞ ቆንጆ ኳስ አመቻችቶ ሲያቀብል ከመሐል ሜዳ መትቶ ለማስቆጠርም ተቃርቦ ነበር።

ፈርናንዴዝ ከጨዋታው በኋላ “ ግብ ማስቆጠር በእርግጠኝነት በእግርኳስ ምርጡ ስሜት ነው “ ብሏል።

አያይዞም “ በሜዳህ እና በደጋፊዎችህ ፊት ሀትሪክ መስራት የሚደንቅ እና የምኮራበት ነው “ ሲል ገልፆታል።

@tikvahethsport          @YisakAH

ተዛማጅ ታሪኮች