ምን አይነት ጨዋታ እንጠብቅ ?

ምን አይነት ጨዋታ እንጠብቅ ?
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በደንብ የተደራጁ በመሆናቸው ጥብቅ እና ጥንቃቄ የተሞላበት ጨዋታ እንደሚሆን ይጠበቃል።
ግብፅ በጨዋታው መሐል ሜዳው ላይ የበላይነቱን በመውሰድ ለሳላህ እና ፈጣን ተጨዋቾቿ ኳስ ለማቀበል ትሞክራለች።
አውስትራሊያ በበኩሏ ወደ ኋላ ተመልሳ መጫወትን በመምረጥ ጠንቃቃ ሆና እንደምትቀርብ ይጠበቃል።
አውስትራሊያ በጨዋታው ከክፍት ጨዋታ ይልቅ ያላትን የተክለ ሰውነት ስጦታ ተጥቅማ በቆመ ኳስ ግብ ለማስቆጠር ትጥራለች።
የአውስትራሊያ ትልቁ ስጋት ሞሀመድ ሳላህ እንደሚሆን ሲጠበቅ ክፍተቶችን ካገኘ ግቦችን ማስቆጠር ይችላል።
የግብፅ ብሔራዊ ቡድን ትልቁ ስጋት አውስትራሊያ በተክለ ሰውነት የተሻለች መሆኗ እና የቆመ ኳስ አጠቃቀሟ ይሆናል።
በዚህም ምክንያት ጨዋታው ብዙ ግቦችን የማንመለከትበት እና የመጀመሪያው ጎል ተፅዕኖ የሚያሳድርበት ሊሆን ይችላል።
ቡድኖቹ ካላቸው የአጨዋወት ቁጥራዊ መረጃ አንፃር የምሽቱ ጨዋታ ወደ መለያ ምት የመሄድ እድልም ይኖረዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe