ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ በ 28 አመት የእግርኳስ ቆይታዬ እንደዚህ አይነት ' ፔናልቲ ' አላየሁም ” አርቴታ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ በ 28 አመት የእግርኳስ ቆይታዬ እንደዚህ አይነት ' ፔናልቲ ' አላየሁም ” አርቴታ
“ በ 28 አመት የእግርኳስ ቆይታዬ እንደዚህ አይነት ' ፔናልቲ ' አላየሁም ” አርቴታ

የመድፈኞቹ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አርሰናል የተሰጠበትን ፍፁም ቅጣት ምት ታይቶ የማይታወቅ ሲሉ ገለፁ።

ከጨዋታዉ በኋላ ቃላቸውን የሰጡት አርቴታ “ ትልቅ ድል ነው ነገርግን የተለየ ሊሆን ይችል ነበር ” ብለዋል።

በምን ምክንያት የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው አርቴታ “ በፍፁም ቅጣት ምቱ ምክንያት " ሲሉ መልሰዋል።

“ በጣም ተበሳጭቻለሁ ተቀባይነት የሌለው ነገር ነው “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

“ ይሄ ሊሆን የማይችል ነገር ነው “ ያሉት አርቴታ “ 28 አመታት በእግርኳስ ቆይቻለሁ ይሄ ፍፁም ቅጣት ምት ሆኖ አላየሁም ” ብለዋል።

አክለውም " ከቃለምልልስ በኋላ ዳኛውን ፈልጌ አናግረዋለሁ “ ሲሉ ማብራሪያ እንደሚጠይቁ ገልጸዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች