ባርሴሎና ሮድሪን ማስፈረም ይፈልጋል !

ባርሴሎና ሮድሪን ማስፈረም ይፈልጋል !
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን የማንችስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪ የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።
ባርሴሎና በዝውውሩ ዙሪያ ከሮድሪ ተወካዮች ጋር ንግግር ማድረጉን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
ሌላኛው የላሊጋ ክለብ ሪያል ማድሪድ አሁንም ሮድሪን ለማስፈረም በመስራት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ የባርሴሎና አጨዋወት ለሮድሪ የሚስማማ በመሆኑ ወደዛ ለማምራት ሊያዘነብል ይችላል ተብሏል።
በተጨማሪም ከስምንት የባርሴሎና ተጨዋቾች ጋር በስፔን ስለነበር መልበሻ ቤቱን በቶሎ እንዲላመድ ሊረዳው ይችላል።
ባርሴሎና ዲ ዮንግን በጉዳት ማጣቱን ተከትሎ አማካይ ለመመልከት ወደ ዝውውር ገበያው ወጥተዋል።
ባርሴሎና ለዝውውሩ ክፍት ቦታ ለማግኘት እና የፋይናንስ ሁኔታውን ለማስተካከል ተጨዋች መሸጥ ሊገደድ እንደሚችል ተጠቁሟል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe