ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ቶተንሀም ማንን እያነጋገረ ነው ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ቶተንሀም ማንን እያነጋገረ ነው ?
ቶተንሀም ማንን እያነጋገረ ነው ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የዝውውር መስኮቱ ሳያበቃ የፊት መስመሩን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል።

ሳቪንሆ የቶተንሀም የረጅም ጊዜ ኢላማ ቢሆንም ማንችስተር ሲቲ ከመሸጡ በፊት ተተኪ ማምጣት ይፈልጋል ተብሏል።

ቶተንሀም በተጨማሪም የሊቨርፑሉን አማካይ ኮዲ ጋክፖ የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ለወኪሎቹ አሳውቀዋል።

ይሁን እንጂ ቶተንሀሞች ከክለቡ ሊቨርፑል ጋር መደበኛ ንግግር እንዳላደረጉ ተገልጿል።

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ኮዲ ጋክፖን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው ተነግሯል።

በተጨማሪም ቶተንሀም ከዚህ በፊት :-

- የፍራንክፈርቱ ጂያን ማቲኦ ባሆያ እና
- የኤሲ ሚላኑ ራፋኤል ሊያኦ ላይ ፍላጎት አሳይተው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች