ቼልሲ በዝውውሩ ምን እየሰራ ነው ?

ቼልሲ በዝውውሩ ምን እየሰራ ነው ?
ሰማያዊዎቹ በዚህ ሳምንት ታይሪክ ጆርጅን ለኤቨርተን በ 18 ሚልዮን ፓውንድ ሸጠዋል።
በሌላ በኩል ማርኮ ፓሌስትራን ያስፈረሙ ሲሆን ግራኒት ዣካን የግላቸው ለማድረግ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም።
ሰማያዊዎቹ አሁን ላይ የራዮ ቫዬካኖውን የግራ መስመር ተሰላፊ ፔፕ ቻቫሪያ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር እየተነጋገሩ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል በዚህ ክረምት ቢያንስ አንድ የመሐል ተከላካይ ስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየም ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የቼልሲ ቀዳሚው ኢላማ የክሪስታል ፓላሱ ላክሮይክስ ሲሆን የኮሞውን ጃኮቦ ራሞን እንደሚያደንቁም ተነግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቼልሲ አሊሀንድሮ ጋርናቾን ለመሸጥ ጥያቄዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ክለቡ ጋርናቾን ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ ለሽያጭ ያቀረበው ሲሆን ቋሚ ዝውውር ብቻ እንደሚቀበል አሳውቋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe