ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

አስቶን ቪላ ሱዙኪን ማስፈረም ይፈልጋል !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
አስቶን ቪላ ሱዙኪን ማስፈረም ይፈልጋል !
አስቶን ቪላ ሱዙኪን ማስፈረም ይፈልጋል !

አስቶን ቪላ ጃፓናዊውን ግብ ጠባቂ ዝዮን ሱዙኪ ከፓርማ ለማስፈረም በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

አስቶን ቪላ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ክለቡን ለመልቀቅ መቃረቡን ተከትሎ ተተኪ ለማስፈረም ንግግር ጀምሯል።

አርጀንቲናዊው ግብ ጠባቂ ማርቲኔዝ ጁቬንቱስን ለመቀላቀል መቃረቡ እየተዘገበ ይገኛል።

ይህንንም ተከትሎ አስቶን ቪላ ሱዙኪን እስከ 30 ሚልዮን ዩሮ ባለው ለማስፈረም እየሰሩ እንደሚገኙ ተነግሯል።

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ሌላኛው የግብ ጠባቂው ፈላጊ ክለብ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ግብ ጠባቂው ፒኤስጂን ለመቀላቀል የሚያደርገው ንግግር መቋረጡን የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች