ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ወርቅ አሳካች !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ወርቅ አሳካች !
ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ወርቅ አሳካች !

በአለም አትሌቲክስ ከ 20ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች።

በሴቶች 3000ሺ ሜትር መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተከታትለው ገብተዋል።

አትሌት አልማዝ ዮሀንስ ውድድሯን 9:15.81 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት በማጠናቀቅ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝታለች።

እንዲሁም አትሌት ወሰኔ አሰፋ 9:30.50 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃ ይዛ በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሸንፋለች።

አትሌት ወሰኔ አሰፋ የአመቱን ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ እስካሁን በውድድሩ አንድ የወርቅ ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ አግኝታለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች