ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ሊጉን አርሰናል ሊያሸንፍ ይችላል ”

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ሊጉን አርሰናል ሊያሸንፍ ይችላል ”
“ ሊጉን አርሰናል ሊያሸንፍ ይችላል ”

የቀድሞ የቼልሲ ተጨዋች ጆን ኦቢ ሚኬል ፕሪሚየር ሊጉን አርሰናል ዳግም ሊያሸንፍ እንደሚችል ገምቷል።

ፕሪሚየር ሊጉን ማን ሊያሸንፍ እንደሚችል የተጠየቀው ጆን ኦቢ ሚኬል “ አርሰናል ጎልቶ ይታያል ” ብሏል።

አርሰናል ከሌሎቹ አንፃር ወጥ ቡድን መሆኑን ያነሳው ጆን ኦቢ ሚኬል “ አሰልጣኙ አብሯቸው የቆየ ነው የራሱን ቡድን ሰርቷል "ሲል ገልጿል።

“ አንዳንዶች የአርሰናልን አጨዋወት ቢተቹም ለውጥ አያመጣም ሊጉን አሸንፏል አሁን ፈተናው ለመድገም ነው “ ሲል ጨምሮ ተናግሯል።

ቀሪዎቹ ሁሉም ቡድኖች አዲስ አሰልጣኝ የሾሙ መሆናቸውን ያነሳው የቀድሞ ተጨዋቹ “ ለዚህ ነው አርሰናልን የምለው " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች