ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ እኛም የማያምር እግር ኳስ መጫወት እንደምንችል አላወቁም “ - ምባፔ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ እኛም የማያምር እግር ኳስ መጫወት እንደምንችል አላወቁም “ - ምባፔ
“ እኛም የማያምር እግር ኳስ መጫወት እንደምንችል አላወቁም “ - ምባፔ

“ በራሳቸው መንገድ አሸንፈናቸዋል ”

የፈረንሳይን ወሳኝ ጎል ያስቆጠረው ኪሊያን ምባፔ ከጨዋታው በኋላ የፓራጓይን የአጨዋወት መንገድ ክፉኛ ተችቷል።

ምባፔ ሲናገርም “ እጃችንን ማቆሸሽ ካለብን እኛም ማቆሸሽ እንችላለን ፤ አጥቅቶ መጫወት የሚያውቅ ቡድን ብቻ አለመሆናችንን አረጋግጠንላቸዋል“ ብሏል።

አክሎም “ ጥሩ እግርኳስ ብቻ ይጫወታሉ ብለው አስበው ነበር ነገርግን የማይረባ እግርኳስ መጫወትም እናውቅበታለን ” ሲል ተደምጧል።

“ ይሄ የእነሱ አጨዋወት ነው በዚህ መንገድ እኛን ለማሸነፍ ሞክረዋል ነገርግን በመጨረሻ በራሳቸው መሳሪያ አሸንፈናቸዋል “ ኪሊያን ምባፔ

ረያን ሸርኪ በበኩሉ “ 30 ጥፋት ሰርተውብን እንዴት አንድ ካርድ ሳይመለከቱ ሊወጡ እንደቻሉ አላውቅም ” ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች