ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ እጩዎች ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ ይችላሉ ” ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ እጩዎች ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ ይችላሉ ” ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ
“ እጩዎች ከዛሬ ጀምሮ መመዝገብ ይችላሉ ” ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ መስከረም 5/2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል።

ምርጫ አስፈፃሚ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት በጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

በዛሬው ዕለት ስራውን የጀመረው ኮሚቴው የእጩዎች ምዝገባ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት አስር ቀናት ይከናወናል ብሏል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በመግለጫው የምርጫውን ቀን ለካፍ እና ፊፋ ማሳወቁን ጨምሮ ገልጿል።

በምርጫው የሚሳተፉት ፕሬዝዳንቶች ብቻ ሲሆኑ ስምንት የስራ አስፈፃሚ አባላት ይኖራሉ ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ የራሱን ስራ አስፈፃሚ ይዞ እንደሚወዳደር ሲገለፅ ሁለቱ ሴቶች መሆን እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች