ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የማንችስተር ሲቲ የዝውውር ሁኔታ ?

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የማንችስተር ሲቲ የዝውውር ሁኔታ ?
የማንችስተር ሲቲ የዝውውር ሁኔታ ?

ጄሬሚ ሞንጋን ከሌስተር ሲቲ የግላቸው ያደረጉት ማንችስተር ሲቲዎቹ ሌላ ወጣት ተጨዋች እየተመለከቱ ይገኛሉ።

ማንችስተር ሲቲ የ 18ዓመቱን ሞሮኳዊ አማካይ አዩብ ቡኣዲ ለማስፈረም እየተመለከቱ መሆኑ ተገልጿል።

ክለቡ ተጫዋቹን ካስፈረመ በኋላ በሊል በውሰት ለማቆየት ወይም በክለቡ ቦታ ለመፈለግ እያጤነ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ማንችስተር ሲቲ የ 23ዓመቱን የቼልሲው ተጨዋች ማሎ ጉስቶ እንደሚያደንቁ ተነግሯል።

ይሁን እንጂ የተጨዋቹ የዝውውር ዋጋ ከፍተኛ መሆኑ ሲገለፅ ለወጥ ከሌለ ሌሎች አማራጮች ሊመለከቱ ይችላሉ ተብሏል።

ሲቲን ማን ይለቃል ?

ማንችስተር ሲቲ በዚህ ሰዓት ከበርናርዶ ሲልቫ ፤ ናታን አኬ ( ገና ያልተጠናቀቀ ) እና ጆን ስቶን ጋር መለያየቱ እርግጥ ሆኗል።

ክለቡ በቀጣይ :-

- ከ ማቲዎ ኮቫቺች
- ሩበን ዲያስ
- ኒኮ ጎንዛሌዝ
- ኦማር ማርሙሽ
- ቲጃኒ ሬንደርስ
- ጄምስ ትራፎርድ እና
- ሳቪንሆ ጋር ሊለያይ እንደሚችል ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲን የሚለቁ ተጨዋቾች ቁጥር አስር ሊደርስ እንደሚችል ሲነገር ሮድሪ ገና ውሉን አላራዘመም።

መረጃው የተገኘው ከ ዘ አትሌቲክ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች