ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን 🏆 ሻምፒዮን ሆነ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን 🏆 ሻምፒዮን ሆነ !
የሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን 🏆 ሻምፒዮን ሆነ !

የ ሲዳማ ቡና ወጣት ቡድን የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል።

ሲዳማ ቡና ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረገውን የየሊጉ ፍፃሜ ጨዋታ በመለያ ምት 3ለ2 ማሸነፍ ችሏል።

ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ነበር ያጠናቀቁት።

በመደበኛው የጨዋታ ጊዜ ለሲዳማ ቡና ዳንኤል ዳዊት እንዲሁም ለወላይታ ድቻ አብርሃም በላይነህ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በአሰልጣኝ አመሀ ዘውዱ የሚመራው የሲዳማ ቡና ከ 20ዓመት በታች ቡድን የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት አንስቷል።

በውድድሩ :-

- ወላይታ ድቻ 2ኛ
- ኢትዮ ኤሌክትሪክ 3ኛ በመሆን የብር እና ነሐስ ሜዳልያ አግኝተዋል።

ሲዳማ ቡና የ 2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ማሸነፉም ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች