የቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ?

የቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ ሁኔታ ?
ሪያል ማድሪድ በዚህ ሳምንት ከቪንሰስ ጁኒየር ተወካዮች ጋር በውል ማራዘም ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል።
ከዚህ ንግግር በኋላ የሪያል ማድሪድ እና ቪንሰስ ጁኒየር የወደፊት ቆይታ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ቪንሰስ ጁኒየር ከዚህ ቀደም ጠይቆ የነበረውን 30 ሚልዮን ዩሮ የሚጠጋ አመታዊ ክፍያ ለመቀነስ ፍቃደኛ መሆኑ ተገልጿል።
ይሁን እንጂ ተጨዋቹ የጠየቀው የፊርማ ጉርሻ ክፍያ ከዚህ በፊት በክለቡ ያልተደረገ እና ችግር መፍጠሩ ተገልጿል።
ሪያል ማድሪድ ሌሎች ተጨዋቾች በተመሳሳይ ይጠይቃሉ በሚል ፍራቻ ያንን ማድረግ አይፈልጉም ተብሏል።
የሪያል ማድሪድ ነባር የበላይ ሀላፊዎች ከስምምነት ካልተደረሰ ቀጣይ በነፃ ላለማጣት በዚህ ወር ቪንሰስ እንዲሸጥ ይፈልጋሉ።
ብራዚላዊው ቪንሰስ በአሁኑ ሰዓት ወደ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን የመጨረሻ ውሳኔውን ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ እንደሚወስኑ ተዘግቧል።
አርሰናሎች ተጨዋቹ ውሉን ለማራዘም ካልተስማማ ለማስፈረም በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
መረጃው የ ዘ አትሌቲክ ነው።
@tikvahethsport @kidusyoftahe