ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ የታዳጊዎችን ጤንነት መጠበቅ አለብን ” ኮሞ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ የታዳጊዎችን ጤንነት መጠበቅ አለብን ” ኮሞ
“ የታዳጊዎችን ጤንነት መጠበቅ አለብን ” ኮሞ

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኮሞ በአካዳሚው ውስጥ አዲስ ህጋ ማውጣቱን አስታውቋል።

ኮሞ ታዳጊ ተጨዋቾች በአካዳሚው ውስጥ በጭንቅላት ኳስ የሚገጩበትን መጠን ቀንሷል።

ክለቡ አዲሱን ህግ ያወጣው “ የታዳጊ ተጨዋቾችን የጭንቅላት ጤና ለመጠበቅ ነው “ ሲል አሳውቋል።

በቀጣይም በክለቡ አካዳሚ ታዳጊዎች በልምምድ እና ጨዋታ ላይ በጭንቅላት ኳስ መምታት አይችሉም ተብሏል።

የክለቡ ከ 10ዓመት በታች ቡድን በጭንቅላት ኳስ መምታት ሲከለከል የማዕዘን ምት በእጅ ውርወራ ይተካል።

ከ 12ዓመት በታች ቡድኑ በወር አንድ ጊዜ ሲፈቀድላቸው ተጨዋቾች ከአምስት በላይ መምታት ይከለከላሉ።

ከ 13ዓመት በታች ቡድኑም የተገደበ ሲሆነ በሳምንት አንድ ጊዜ እንደሚፈቀድላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች