ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

የቶተንሀም ስፖንሰር ውሉን አቋረጠ !

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
የቶተንሀም ስፖንሰር ውሉን አቋረጠ !
የቶተንሀም ስፖንሰር ውሉን አቋረጠ !

ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን እያሳለፈ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ስፖንሰሩን አጥቷል።

የቶተንሀም ይፋዊ የፈርኒቸር ስፖንሰር ሲዲዝ ከቶተንሀም ጋር ያለውን ኮንትራት ማቋረጡ ተገልጿል።

ተቋሙ ከቶተንሀም ጋር ያለውን ስምምነት የውል ማቋረጫ አንቀጽ ተጠቅሞ እንደሚያቋርጥ ተነግሯል።

ተቋሙ ውሉን የሚያቋርጠው ቶተንሀም ደካማ የውድድር ዘመን ጅማሮ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።

እስካሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለው ቶተንሀም በሊጉ በሁለት ነጥብ ሃያኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች