የጨዋታ ቀን 🇪🇹

የጨዋታ ቀን 🇪🇹
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ከሴኔጋል ጋር የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ጨዋታውን ያደርጋል።
የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሲል በባሕር ዳር ስታዲየም መካሄድ ይጀመራል።
በኢትዮጵያ በኩል ማን አይሳተፍም ?
በዛሬው ጨዋታ በረከት ወልዴ በጉዳት እንዲሁም መስፍን ታፈሰ በቅጣት እንደማይሰለፉ ተገልጿል።
ጨዋታውን ማን ይመራል ?
ካፍ ካሜሮናዊው ዳኛ ዊሊ ሴቴፋን ንጋህ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት እንዲመሩ መርጧል።
ዋና ዳኛው አምና የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ቡድን ከሞሮኮ ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ መርተው ነበር።
የጨዋታው ትኬት የት ይገኛል ?
ጨዋታውን ለመከታተል የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባዘጋጀው ሊንክ " eff-tickets.com " ትኬት መቁረጥ ይቻላል።
እንዲሁም በአካል ቲኬት መግዛት ለሚፈልጉ በአዝዋ ሆቴል በኩል በሚገኘው የመግቢያ በር እየተሸጠ ይገኛል።
ጨዋታውን በምን መከታተል ይቻላል ?
ጨዋታውን በዲኤስቲቪ ቻናል ቁጥር 227 በጎጅ ፓኬጅ እና ሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል ይቻላል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe