ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

“ ጥራት ያላቸውን ተጨዋቾች ለማምጣት በትኩረት እየሰራን ነው ” ሚኬል አርቴታ

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
“ ጥራት ያላቸውን ተጨዋቾች ለማምጣት በትኩረት እየሰራን ነው ” ሚኬል አርቴታ
“ ጥራት ያላቸውን ተጨዋቾች ለማምጣት በትኩረት እየሰራን ነው ” ሚኬል አርቴታ

የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በዝውውር መስኮቱ ገና ስራውን እንዳላጠናቀቀ ገልፀዋል።

በዚህ ሳምንት የብሩኖ ጉማሬሽን ዝውውር ያጠናቀቀው አርሰናል በቀጣይ ተጨማሪ እንቅስቃሴ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

“ ማድረግ የምንፈልገው ተጨማሪ ነገር አለ ” ያሉት አርቴታ “ ቡድኑን ተሰጥኦ እና ጥራት ባላቸው ተጨዋች ማጠናከር አለብን "ብለዋል።

ይህንን ለማሳካትም “ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነው ” ሲል ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

አክለውም “ ፍላጎቱ በእኛ ላይ ብቻ የተመረኮዘ ባለመሆኑ ቃል መግባት አንችልም “ ብለዋል።

“ እውነተኛ ልዩነት መፍጠር የሚችሉ እና ደረጃችንን ማሻሻል የሚችሉ የተወሰኑ ተጨዋቾች አሉ ” አርቴታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች