ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#AddisAbabaCityCup 🇪🇹

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#AddisAbabaCityCup 🇪🇹
#AddisAbabaCityCup 🇪🇹

የ 2019 የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ከመስከረም 9-26/2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል።

ውድድሩ በስድስት የአዲስ አበባ ከተማ እና ሁለት ተጋባዥ ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ የከተማዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ገልጿል።

በውድድሩ :-
- ቅዱስ ጊዮርጊስ
- ኢትዮጵያ ቡና
- መቻል
- ኢትዮጵያ መድን
- ኢትዮ ኤሌክትሪክ
- ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
- አዳማ ከተማ እና
- ጋሞ ጨንቻ እንደሚሳተፉ ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከቫርዳስ  ኢንተርቴይመንት እና ኒዮ ማርኬቲንግ ጋር የሶስት አመት የኮሜርሻል መብት ሽያጭ ስምምነት ተፈራርሟል።

የከተማዋ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከዚህ ስምምነት 45 ሚሊዮን ብር የሚያገኝ ይሆናል።

ውድድሩ ከመስከረም 9-26/2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች