ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#WorldCup2026

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#WorldCup2026
#WorldCup2026

ዛሬ በሚካሄድ የ 2026 አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ስፔን ከ ቤልጅየም ጋር ይጫወታሉ።

ሁለቱ ቡድኖች ምሽት 4:00 ሰዓት በካሊፎርንያ ሎስ አንጀለስ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ጨዋታውን እንግሊዛዊው ዳኛ ማይክል ኦሊቨር በመሀል ዳኝነት እንዲመሩት ተመርጠዋል።

ስፔን በውድድሩ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች አንዴም መረቧን ሳታስደፍር ለሩብ ፍፃሜ ደርሳለች።

ስፔን በተከታታይ ስድሰት የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ግብ ያልተቆጠረባት የመጀመሪያዋ ሀገርም ሆናለች።

ቤልጂየም በበኩሏ በውድድሩ በርካታ ግብ ያስቆጠረች ሁለተኛዋ ሀገር ሆና ለጨዋታው ትቀርባለች።

የሁለቱ ቡድኖች አሸናፊ በግማሽ ፍፃሜው ከፈረንሳይ ጋር የሚጫወት ይሆናል።

የትኞቹ ተጨዋቾች አይገኙም ?

በቤልጅየም ቡኩል አማዱ ኦናና በከባድ ጉዳት ምክንያት ከውድድሩ ውጪ መሆኑ ይታወቃል።

በስፔን በኩል ጨዋታው ያመልጠዋል ተብሎ የሚጠበቅ ተጨዋች የለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች