ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#WorldCup2026

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#WorldCup2026
#WorldCup2026

የ አለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ሲጀምሩ ሞሮኮ ከፈረንሳይ ይገናኛሉ።

ሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታቸውን በቦስተን ስታዲየም ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ ያደርጋሉ።

ጨዋታውን አርጀንቲናውያን ዳኞች በጋራ በመሆን ይመሩታል።

አሸናፊው ብሔራዊ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው የስፔን እና ቤልጂየምን አሸናፊ ይገጥማል።

የእርስበርስ ግንኙነት ?

ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በ 2022 አለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ሲሆን ፈረንሳይ 2ለ0 አሸንፋ ነበር።

አጠቃላይ ስድስት ጊዜ ሲገናኙ ፈረንሳይ አራቱን ስታሸንፍ በቀሪዎቹ አቻ ተለያይተዋል።

ለቅጣት የተቃረቡ ተጨዋቾች ?

በሞሮኮ በኩል ኢሳ ድዮፕ ፣ ሀኪሚ ፣ ሬድዋን ሀልሀል እና ኤል ሀኑስ በፈረንሳይ በኩል ማኑ ኮኔ እና ኦሊሴ ቢጫ ካርድ ካዩ አንድ ጨዋታ ይቀጣሉ።

የትኞቹ ተጨዋቾች አይገኙም ?

በሞሮኮ በኩል እስማኤል ሳይባሪ ከጨዋታው ውጪ ሲሆን በፈረንሳይ በኩሉ ቹዋሜኒ በጉዳት መድረሱ አጠራጣሪ ነው።

ሞሮኮ ጨዋታውን ካሸነፈች በተከታታይ ለሁለተኛ ጊዜ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ በመሆን በታሪክ የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለች።

ፈረንሳይ በበኩሏ ካሸነፈች በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ የግማሽ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆን ትችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች