ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

#WorldCup2026

ምንጭ፦ TIKVAH | Ethiopia Sport

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
#WorldCup2026
#WorldCup2026

ቤልጅዬም በሰፊ የጎል ልዩነት 5ለ1 ኒውዝላንድ አሸንፋ የምድቡ የበላይ ሆና አጠናቃለች።

ትሮሳርድ 2X ፣ ዴብሮይን ፣ ሉካኩ እና ሴልሜከር ቤልጅዬምን አሸናፊ ያደረገች ግብ አስቆጥረዋል።

ግብፅ እና ኢራን 1ለ1 በተለያዩበት መርሐ ግብር ግብፅ ሁለተኛ በመሆን ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች።

በጨዋታው ሞሀመድ ሳላህ ባስተናገደው ጉዳት ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

ግብፅ በጥሎ ማለፉ ከ አውስትራሊያ ጋር መርሐ ግብሯን የምታደርግ ይሆናል።

ኢራን ጥሩ ሶስተኛ ሆና የማለፍ እድል ሲኖራት የሌሎች ሀገራትን ውጤት ለመጠበቅ ትገደዳለች።

በምድቡ የተመዘገበውን ውጤት ተከትሎ ሴኔጋል 🇸🇳 በይፋ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

ምንም ጨዋታ ማሸነፍ ያልቻለችው ኒውዝላንድ የምድቡ ተሰናባች ሀገር ሆናለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe

ተዛማጅ ታሪኮች