" ሁኔታዎች ሲስተካከሉ አየር መንገዱ በ24 ሰዓት ውስጥ በረራዎችን በድጋሚ ለማስጀመር ዝግጁ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ሁኔታዎች ሲስተካከሉ አየር መንገዱ በ24 ሰዓት ውስጥ በረራዎችን በድጋሚ ለማስጀመር ዝግጁ ነው " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ (ለቲክቫህ ኢትዮጵያ)
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ዳግም የሚጀምርበት ቀን እስካሁን ድረስ እንዳልተወሰነ የአየር መንገዱ ከፍተኛ ኃላፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በአየር መንገዱ የቲኬት መቁረጫ የኦንላይን ሲስተም ላይ ከጥቅምት 15 (October 25, 2026) ጀምሮ ወደ መቐለ የሚደረጉ በረራዎች ክፍት ሆነው መታየታቸውን ተከትሎ በርካታ ደንበኞች በረራው ዳግም ሊጀመር ስለመሆኑ ጥያቄ ሲያነሱ ነበር።
በጉዳዩ ዙሪያ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የአየር መንገዱ የበላይ ኃላፊ በሰጡት ማብራሪያ፣ በሲስተሙ ውስጥ የሚታየው የ ኦክቶበር 25 በረራ አስቀድሞ በሲስተም የተያዘ በመሆኑ እንጂ በረራው ይጀመራል ተብሎ እንዳልሆነ ገልጸው፣ መረጃው ከሲስተም እንዲወጣ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
አየር መንገዱ የበረራ መርሃ-ግብር (Schedule) ማውጣት ያልቻለው የአውሮፕላን ማረፊያው (Airport) እስካሁን በአየር መንገዱ ቁጥጥር ስር ስላልሆነና በአካባቢው ለመስራት ባለመቻሉ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፣ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ቢያንስ የአንድ ወር ጊዜ ለመስጠት በመታሰቡ እስከ ጥቅምት 21 (October 31) ድረስ ምንም አይነት በረራ እንደማይኖር ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ ምቹ የሥራ ሁኔታዎች ከተፈጠሩና ነገሮች ከተስተካከሉ አየር መንገዱ በ24 ሰዓት ውስጥ በረራዎችን በድጋሚ ለማስጀመር ዝግጁ መሆኑን ኃላፊው ጨምረው አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ወደ መቐለ ፣ አክሱም እና ሽሬ የሚያደርገውን በረራ ከመስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው ማቋረጡን ማሳወቁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia