" ማስተር ፕላኑ 30.65 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብሔራዊ የኢንቨስትመንት ፍላጎትን አሳይቷል " - አገልግሎቱ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ማስተር ፕላኑ 30.65 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብሔራዊ የኢንቨስትመንት ፍላጎትን አሳይቷል " - አገልግሎቱ
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት (EEU) የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እና የዲጂታል አሠራርን ለማጠናከር ያዘጋጀውን የ25 ዓመት ብሔራዊ የዲስትሪብዩሽን ሥርዓት ማስተር ፕላንና የማስፋፊያ ጥናት ይፋ አድርጓል።
ከ2024 እስከ 2049 የሚቆየው ይህ ዕቅድ፣ በዓለም ባንክ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በመላ ሀገሪቱ 79,000 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመሮች፣ 1,100 መጋቢ መስመሮች እና 183 ሰብስቴሽኖች ላይ የተካሄደ ዳሰሳን መሠረት አድርጓል።
በጥናቱ መሠረት ከ1,100 መጋቢ መስመሮች ውስጥ 271 የኃይል መሸከም አቅማቸው በቂ እንዳልሆነ የተገኘ ሲሆን፣ 182 መስመሮች ደግሞ ከፍተኛ የኃይል ጭነት እንዳለባቸው ተመልክቷል።
በተጨማሪም 6,800 ትራንስፎርመሮችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የኔትወርክ መሠረተ ልማቶች ጥገናና ማሻሻያ እንደሚያስፈልጋቸው ተለይቷል። ለእነዚህ የአፋጣኝ ማስተካከያ ሥራዎች 71 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።
ጥናቱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ፍላጎት በፍጥነት እንደሚጨምር ያመለክታል። በ2030 10,493 ሜጋዋት እንደሚደርስ የተተነበየው የኃይል ፍላጎት፣ በ2049 ወደ 39,327 ሜጋዋት እንደሚያድግ ተገልጿል።
አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ ሲጠቁም፣ የአዲስ አበባ የኃይል ፍላጎት በ2025 ከ1,608 ሜጋዋት ወደ 16,057 ሜጋዋት በ2049 እንደሚያድግ ተተንብዮአል።
እስከ 2027 በሚተገበሩ የአጭር ጊዜ ፕሮጀክቶች 16,511 ኪሎ ሜትር አዲስ መስመር ዝርጋታ፣ 9,676 ኪሎ ሜትር የነባር መስመር ማሻሻያ፣ 10,603 አዳዲስ ትራንስፎርመሮች ተከላ እና 11,174 ነባር ትራንስፎርመሮች የአቅም ማሳደግ ሥራዎች ይካሄዳሉ። ለእነዚህ ብቻ 1.33 ቢሊየን ዶላር በጀት ያስፈልጋል።
እስከ 2049 በመላ ሀገሪቱ 128 አዳዲስ ሰብስቴሽኖች እንዲገነቡ የታቀደ ሲሆን፣ ለዚህና ለተያያዥ ሥራዎች 16.3 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል። በተጨማሪም ስማርት ሜትሮች፣ SCADA፣ ዲስትሪብዩሽን አውቶሜሽን፣ GIS እና ዘመናዊ የዳታ ማዕከላትን የሚያካትት የ10 ዓመት ስማርት ግሪድ ስትራቴጂም ተዘጋጅቷል፤ ለዚህ 515 እስከ 640 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ይጠይቃል።
ለአዲስ አበባና ሸገር ከተሞች ብቻ እስከ 2049 የኃይል ፍላጎትን ለማሟላት 207 አዳዲስ ሰብስቴሽኖች እና ተጨማሪ የትራንስፎርመር ማስፋፊያዎች እንደሚያስፈልጉ በመግለጽ፣ 2.81 ቢሊየን ዶላር በጀት እንደሚያስፈልግ ጥናቱ ያሳያል።
በአጠቃላይ የ25 ዓመቱ ማስተር ፕላን ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር 30.65 ቢሊየን ዶላር ብሔራዊ ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። ይህ በጀት የኔትወርክ ማሻሻያና ማስፋፊያ፣ የሰብስቴሽን ግንባታ፣ የSCADA/DMS ሥርዓት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ማሻሻያ፣ የስማርት ግሪድ እና የዘመናዊ ቆጣሪዎች ኢንቨስትመንትን ያካትታል።
ተጨማሪ፦ https://www.facebook.com/share/p/1QfBDtopdM/
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ሃምሌ 20 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia