ሰዎችን በማገት የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላትና የመንግስት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ሰዎችን በማገት የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላትና የመንግስት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በባህር ዳር በሰዎች ላይ እገታ በመፈፀም፣ ገንዘብ በመጠየቅና በመቀበል ወንጀል የተሳተፉ የወንጀል ቡድን አባላት እና ለወንጀሉ መፈፀሚያነት የዋለ የመንግሥት ተሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የባህርዳር ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪውቹ ታጋቾቹን አፍነው በመውሰድ ለ11 ቀናት አግተው ያቆዩዋቸው ሲሆን ፤ በወቅቱ ታጋቾቹን ለመልቀቅ 3 ሚሊዮን 370 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው በመጠየቅና ገንዘቡ ከተከፈላቸው በኋላ እንዲለቀቁ ማድረጋቸውን የምርመራ መረጃው ያመላክታል።
እንደ ፖሊስ መረጃ፣ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 (ኤፍራታ) አካባቢ ነዋሪና ነጋዴ የሆኑ ሶስት ግለሰቦች በራሳቸው ተሽከርካሪ ወደ ስራ ቦታቸው በመሄድ ላይ እያሉ በወቅቱ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት እገታ ተፈፅሞባቸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ታጋቾቹን በመንግስት ተሽከርካሪ አፍነው በመውሰድ ለ11 ቀናት አግተው ያቆዩ ሲሆን የወንጀሉ አደራጆች እና ተሳታፊዎች በቅንጅት የሰሩ ነበሩ።
በተደረገው ክትትልም ፦
1ኛ. ወንጀሉን በዋናነት ያስተባበረው አብርሃም ጫኔ የተባለ በቀበሌ 06 የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ባለቤት፤
2ኛ. የመንግሥት ተሽከርካሪን ለወንጀል ያዋለ መለሰ ጌትነት የተባለ አሽከርካሪ ግለሰብ፤
3ኛ. ታጋቾቹን ደብቆ ያቆየውና ወንጀሉን የሸፈነው በቀበሌ 14 እንዘግድብ አካባቢ የሚገኝ ህንፃ አስተዳዳሪ (170 ሺህ ብር ክፍያ በመቀበል ወንጀሉን ያደባበሰ)፤
4ኛ. አበበ ጌቴ፣ ከአዲስ አበባ የተሳተፈ ተባባሪን ጨምሮ እስከ 870 ሺህ ብር በባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ ረገድ የተሳተፉ አባላት፤ በአጠቃላይ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በተጨማሪም ለወንጀሉ ማስፈፀሚያነት የዋሉ አንድ ማካሮቭ እና አንድ ክላሽንኮቭ የጦር መሳሪያዎች ከነተሽከርካሪው ተይዘዋል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ተቋማት ለስራ የተመደቡላቸውን ተሽከርካሪዎችና አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስቧል።
በአሁኑ ወቅት ቀሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚያስችል የምርመራ ስራ መቀጠሉን ፖሊስ ገልጿል።
#AmharaPolice
ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia