በሞጆ በ60 ሄክታር ላይ የተገነባው ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተመረቀ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በሞጆ በ60 ሄክታር ላይ የተገነባው ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተመረቀ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሞጆ በ60 ሄክታር መሬት ላይ የተገነባውን ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከል ማስፋፊያ የመጀመሪያ ምዕራፍ ማስመረቃቸውን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕከሉ ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስኬት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ፕሮጀክቱ በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ባለ20 ጫማ ኮንቴነሮችን ማስተናገድ የሚችሉ ጣቢያዎችንና ዘመናዊ መጋዘኖችን ያካተተ ነው።
ማዕከሉ የደረቅ ብትን ጭነቶችን በሀገር ውስጥ ማሸግ እንዲቻል በማድረግ የውጭ ምንዛሬን ከመቆጠብ ባለፈ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።
የማዕከሉን የአሰራር ፍጥነት ለማሳደግ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተተከለው የባቡር ላይ ክሬን ከባቡር መስመር ጋር የሚደረገውን የኮንቴነር ዝውውር በከፍተኛ ፍጥነት ያከናውናል።
ሙሉ የማዕከሉ አሰራር በዘመናዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት የተሳሰረ በመሆኑ ለተገልጋዮች ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ለማቅረብ እንደሚያስችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ማዕከሉ ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር ባሻገር ኢትዮጵያን፣ ደቡብ ሱዳንን እና ዩጋንዳን የሚያስተሳስረው የ‘ደሱ’ ኮሪደር አካል መሆኑም ተጠቁሟል።
ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ ያላትን ስፍራ ከማሻሻል ባለፈ የቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ወደ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ የሚያሸጋግር እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።
ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia