" በተኩስ ነው ያስቆሟቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ ተቃጠሉ፤ ታጣቂዎቹ አመለጡ። ከ8 በላይ ሾፌሮች ታግተዋል። ብዙ ነዳጅ ጫኝ መኪናዎች ተቃጥለዋል፤ አንድ ሹፌር ብቻ ነው ያመለጠው " - ማህበሩ
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" በተኩስ ነው ያስቆሟቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ ተቃጠሉ፤ ታጣቂዎቹ አመለጡ። ከ8 በላይ ሾፌሮች ታግተዋል። ብዙ ነዳጅ ጫኝ መኪናዎች ተቃጥለዋል፤ አንድ ሹፌር ብቻ ነው ያመለጠው " - ማህበሩ
👉 " በእነዚህ ተግባራት የተሰማራችሁ ማንኛችሁም አካላት እባካችሁ ሾፌሮችን አትግደሏቸው፤ አታግቷቸው! "
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከስምንት በላይ ሾፌሮች ታግተው ሲወሰዱ፣ በርካታ ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቃጠላቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ሾፌሮች፣ ረዳቶችና ተሳፋሪዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን በየእለቱ የሚከታተለው "የሾፌሮች አንደበት" በበኩሉ፣ ጥቃቱ ስለመፈጸሙ መረጃ እንደረሰው አስታውቆ፣ የታጋቾችን ብዛት 14 አድርሶታል።
ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ሲቃጠሉ የሚያሳይ ምስል ከስፍራው የወጣ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ በበኩላቸው፣ ጥቃቱን የተመለከተ መረጃ እንደደረሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
እሳቸው በሰጡን ቃል፣ " በደንቢ ዶሎ በኩል ወደ አሶሳ ሲጓዙ የነበሩ አብዛኛዎቹ ነዳጅ ጫኝ የሆኑ ተሽርካሪዎች በታጣቂዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ብዙ ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል። ከ8 በላይ ሾፌሮች ታግተዋል። አንድ ሹፌር ብቻ ነው ያመለጠው " ብለዋል።
በደረሳቸው መረጃ መሰረት ሁነቱን ሲያስረዱ፣ " በተኩስ ነው ያስቋሟቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ ተቃጠሉ፤ ታጣቂዎቹ አመለጡ። ይህ የሆነው ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም ነው " ሲሉ ተናግረዋል። " ወዲያው ስልክ ተደወለልን፤ ጉዳዩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል አሳውቀናል። ክትትል እያደረጉ ነው " ያሉት አቶ ሰለሞን፣ ታጣቂዎቹ ታጋቾቹን ምን እንዳደረጓቸው እንዳልታወቀ ተናግረዋል።
የታገቱት ስምንት ሾፌሮች ከሆኑ ተሽከርካራዎቹ ስምንት ናቸው ማለት ነው?ተብሎ ሲጠየቁ፣ " ተሽከርካሪዎቹ ዘጠኝ ሳይሆኑ አይቀሩም፤ እርግጠኛ አይደለሁም " ብለው፣ የታገቱት ሾፌሮች አብሯቸው ረዳት ካለ የታጋቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበርን ስለጉዳቱ መጠን ለመጠየቅ የሞከረ ሲሆን ማህበሩ፣ "ስለእርሱ ጉዳይ ምንም መረጃ የለንም" ብሏል። ጥቃቱ የደረሰበት አካባቢ አመራሮችን ለማግኘት አልተቻለም። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ለማነጋገር ሙከራ ቢደረግም የስልክ ሆነ የፅሑፍ ምላሽም አልተገኘም።
በምዕራብ ወለጋ ዞን "ጊምቢ" እና "ቢላ" መካከል "ብዙ አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል የሚል መልዕክት ደርሶናል። በርካታ ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተቃጥለዋል" ሲል ያስታወቀው "የሾፌሮች አንደበት" ከቆይታ በኋላ ባጋራው መረጃ ደግሞ ቢያንስ "14 ሾፈሮች" ታግተው መወሰዳቸውን ገልጿል።
ጥቃት አድራሾቹ፣ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ/ም "የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎችን ከማቃጠላቸው ባለፈ አሽከርካሪዎችን አፍነው ወስደዋል፤ ይህ እጅግ አላዋቂነት የጎላበት ጭካኔ የተሞላበት ተግባር ነው" ሲል ድርጊቱን አውግዟል።
"ትናንት በአሽከርካሪ ላይ የሚፈፀምን እገታ ማስቆም ሲቻል ቆሞ መመልከት ዛሬ በዚህ ልክ ጉዳት፣ ውድመት እንዲደርስ በርን ከፍቷል" ሲልም ወቅሷል።
በተያያዘ፣ በ2017 ዓ/ም የተፈጸሙ ጥቃቶችን ያጋራ ሲሆን፣ በዚህም 116 ሾፌሮች፣ ረዳቶች እና ተሳፋሪዎች መገደላቸውን ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት ጭምር ጠቅሶ መረጃ አጋርቷል። ከሟቾች በተጨማሪ 608 ሾፌሮች፣ ረዳቶችና ተሳፋሪዎች በተለያዩ ቦታዎች መታገታቸውን አስታውቋል። እነዚህ ጥቃቱን የተመለከቱ ቁጥሮች "ለሾፌሮች አንደበት" የደረሱ ብቻ መሆናቸውንም አስገንዝቧል።
የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ምን መልዕክት አስተላለፈ ?
"ሹፌር ምን አደረገ? ለምንድን ነው የሚገደለው፤ የሚታገተው? በዚህ ተግባር የተሰማራችሁ ማንኛችሁም አካላት እባካችሁ ሾፌሮችን አትግደሏቸው፤ አታግቷቸው። ምንም አላጠፉም። ህይወታቸውን፣ ደማቸውን፣ ላባቸውን እየሰጡ ነው ያሉት።
ሹፌር ለሀገር የሚሰጠው አገልግሎት ከማንኛውም በላይ ነው። እባካችሁ ሾፌሮች በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ሁሉ ድጋፍ እና ክትትል፣ ቁጥጥር አድርጉላቸው። ነዳጅ፣ መድኃኒት፣ ማዳበሪያ፣ ምግብ፣ የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ነው ለህዝብ የሚያጓጉዙት። በህዝብ ትራንስፖርትም ህዝብ ነው የሚያጓጉዙት። ተቀጣሪዎችም ናቸው።
አሽከርካሪዎቻችንን እያስገነዘብን በሌሊት፣ የጸጥታ ችግር ባለበት ቦታ በሚያደርጉት ጉዞ መረጃ አጣርተው እንዲሆን አድርገን ጥቃቱ በተወሰነ መልኩ ረግቦ ነበር። አሁን ደግሞ ጥቃት ተፈጸመ" ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ጰጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia