ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ከ12 ሰዓታት በላይ የቆየ የደን ቃጠሎ ጉዳት አደረሰ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ከ12 ሰዓታት በላይ የቆየ የደን ቃጠሎ ጉዳት አደረሰ።
በትግራይ እና ዓፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ከ12 ሰዓታት በላይ የቆየ የደን ቃጠሎ ጉዳት አደረሰ።

ቃጠሎው ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን፣ ፃዕዳ እምባ ወረዳ፣ ከዓፋር ክልል ዳሉል ወረዳ ጋር በሚዋሰነው የሐዊለ ቀበሌ አካባቢ መነሳቱን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።

በእሳቱ 4.125 ሄክታር የሚገመት ደንና የግጦሽ ሳር መውደሙ ተገልጿል። በተለይም የገራህቲ ጥብቅ ደን በቃጠሎው ጉዳት ደርሶበታል።

የቃጠሎው መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፣ ምክንያቱን ለማጣራት ምርመራ መጀመሩ ታውቋል።

የትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን አስተዳደር እንዳስታወቀው በአካባቢው ነዋሪዎች ባህላዊ የእሳት ማጥፊያ ዘዴዎች በመጠቀም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡30 ላይ ቃጠሎው ሙሉ በሙሉ ማስቆም ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች