በአማራ ክልል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ውጭ የነበሩትን ህጻናት በበቂ ሁኔታ ተቀብለው ለማስተማር የሚያስችላቸው ሁኔታ ላ…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

በአማራ ክልል በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች የሚገኙ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ውጭ የነበሩትን ህጻናት በበቂ ሁኔታ ተቀብለው ለማስተማር የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ አይገኙም ተባለ።
የአማራ ክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት (ARCSOC) በክልሉ ያለውን የትምህርት ሁኔታ በሚመለከት መግለጫ አውጥቷል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በደረሰው በእዚህ መግለጫ ምክር ቤቱ ጥራት ያለው ትምህርት በእኩልነት የማግኘት መብት የሰብዓዊ መብትና የማህበራዊ ፍትህ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ፣ በአማራ ክልል ባለፉት 3 ዓመታት በተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ዘርፉ በተለያዩ መልኩ ጉዳት እየደረሰበት መሆኑን አመልክቷል።
ተቋሙ ባለፉት ሦስት አመታት በግጭት ውስጥ በቆየው አማራ ክልል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው እንዲገለሉ ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ይህም በህጻናቱ የትምህርት እድል፣ በአካዳሚክ እድገታቸው እና በወደፊት እድገታቸው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል ነው ያለው።
እንደ መግለጫው ከሆነ፣ በ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን መመዝገብ ከነበረባቸው 7.4 ሚሊዮን የክልሉ ተማሪዎች መካከል የተመዘገቡት 4.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ብቻ ነበሩ።
ይህም ማለት 3.1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ከትምህርት ወይም ከምዝገባ ውጭ ሆነው መቆየታቸውን የሚያመላክት መሆኑን ያመላከተው ምክር ቤቱ "ይህ ቁጥር በየዓመቱ ወደ ትምህርት ዕድሜ የሚገቡ አዳዲስ ህጻናትን ሳያካትት መሆኑ ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል" ነው ያለው፡፡
በክልሉ በቀጠለው ግጭት ወይም ጦርነት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ከመደበኛ ሥራቸው ውጭ ሆነዋል ያለ ሲሆን ከእነዚህም መካከል :-
- በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ለወታደራዊ ካምፕ ወይም ለተፈናቃዮች መጠለያ ሆነው መቆየታቸውን
- በግጭቱ ምክንያት ብዙ ትምህርት ቤቶች መፍረሳቸው ወይም መጎዳታቸው እንዲሁም የመማሪያና የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን ማጣታቸው ተጠቅሷል።
የ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ዝግጅትን በተመለከተም በግጭቱ ውስጥ የሚሳተፉ ወገኖች ትምህርት እንዲጀመር በይፋ እየቀሰቀሱ መሆናቸውን እና አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ከወታደራዊ ካምፕነት ነፃ እንዲሆኑ መደረጉን እንዲሁም የምዝገባ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ሰምተናል ያለው ተቋሙ ለዚህም በጎ አስተዋጽኦ ለሚመለከታቸው አካላት ምስጋና አቅርቧል።
ይሁን እንጂ ምክር ቤቱ አለኝ ባለው መረጃ መሠረት፣ አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከትምህርት ውጭ የነበሩትን ህጻናት በበቂ ሁኔታ ተቀብለው ለማስተማር የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ አይገኙም ብሏል።
የተወሰኑት ፈርሰዋል፣ ሌሎች ደግሞ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመማሪያ መጽሐፍትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ይጎድላቸዋል በማለትም አክሏል።
ስለሆነም ምክር ቤት የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም የክልሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት እንዲጀመር ከፖለቲካዊ እና ወታደራዊ አጀንዳዎች ነፃ እንዲደረጉ ሲል በግጭት/በጦርነት ውስጥ ላሉ ሁሉም ወገኖች ጥሪውን አቅርቧል።
በተጨማሪም ወላጆች ከስጋት ነጻ ሆነው ልጆቻቸውን እንዲልኩ፣ ህጻናትም ያለስጋት እንዲማሩ፣ ትምህርት ቤቶችን እና አካባቢያቸውን ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንዲደረጉ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ መምህራንን እና ተማሪዎችን ከጥቃት እንዲጠበቁ እና ትምህርት የፖለቲካና የጦርነት አጀንዳ መሳሪያ እንዳይሆን እንጠይቃለን ብሏል።
ለቀጣይነቱም ይህ እንዳይሆን የሚያጣራ እና የሚከታተል ሁሉም ወገኖች ያመኑበት ( ከወላጆች፣ ሀገር ሽማግሌዎች፥ ከሀያማኖት አባቶች እና ከሀገር በቀል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተውጣጣ) ገልተኛ አካል እንዲቋቋምም ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
የአማራ ክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ከ400 በላይ አባል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ያቀፈ የአማራ ክልል ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካይ ተቋም ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia