ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

በአዲስ አበባ የመብራት መሠረተ ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል መጨመሩ ተገለጸ።

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
በአዲስ አበባ የመብራት መሠረተ ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል መጨመሩ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ የመብራት መሠረተ ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል መጨመሩ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን፣ በከተማዋ በከፍተኛ ወጪ በተዘረጉ የመብራት መሠረተ ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል በተደጋጋሚ እየተፈጸመ መሆኑን ገለጸ።

በተለይም ፦
- ቦሌ ቡልቡላ ካርጎ ጀርባ፣
- ሲኤምሲ፣
- ሀይሌ ጋርመንት–ሀጫሉ መንገድ፣
- መገናኛ 24፣
- ቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ፣
- ካሳንቺ ሰማኸኝ ድልድይ
- ከጉለሌ እስከ 6 ኪሎ የኮሪደር ልማት አካባቢዎች ላይ ስርቆቱ እየተስፋፋ መሆኑን አመልክቷል።

በስርቆቱ ከሚወሰዱት ንብረቶች መካከል ኬብሎች፣ ቆጣሪዎች፣ ብሬከሮችና ሌሎች የመብራት መሠረተ ልማት እቃዎች ይገኙበታል።

ባለስልጣኑ፥ ህብረተሰቡ እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት የመብራት መሠረተ ልማቶቹን በቅንጅት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርቧል።

የመብራት ስርቆት ወይም ተያያዥ ጉዳይ ካዩ በነፃ የስልክ ጥሪ 9101 በመደወል ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 10 ቀን 2018 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች