☕️ 1 ዩሮ ወደ 11.20 ዩሮ ፦ አውሮፓ እሴት ባልተጨመረበት ቡና የምታገኘው ግዙፍ ትርፍ !
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

☕️ 1 ዩሮ ወደ 11.20 ዩሮ ፦ አውሮፓ እሴት ባልተጨመረበት ቡና የምታገኘው ግዙፍ ትርፍ !
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልከው አጠቃላይ ቡና ውስጥ 34 በመቶ የሚሆነው መድረሻው የአውሮፓ ገበያ መሆኑን «የቡና ምጣኔ ሀብታዊ ተፅዕኖ በአውሮፓ» (Economic Impact of Coffee in Europe) የተሰኘ ጥናት ይፋ አድርጓል።
ይህንን የቡና ኢኮኖሚ የዳሰሰ ጥናት ያጠናው በዩናይትድ ኪንግደም (እንግሊዝ) የሚገኘው «አውሮፓ ኢኮኖሚክ ሪሰርች ሊሚትድ» (European Economic Research Limited) የተባለ ተቋም ነው።
ሰነዱ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራትን ጨምሮ እንግሊዝ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድን ያካተተ ሰፊ ቀጠናን የተመለከተ ነው።
በጥናቱ መሠረት እ.ኤ.አ. በ2024 የአውሮፓ ሀገራት ከኢትዮጵያ 523.6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ቡና ያስገቡ ሲሆን፣ ይህም ለአውሮፓ አጠቃላይ የቡና ገቢ ንግድ (Import) 3.4 በመቶውን ብቻ የሚሸፍን ቢሆንም፣ ለኢትዮጵያ ግን አጠቃላይ የውጭ ሸቀጥ ሽያጭ 11.8 በመቶውን የሚሸፍን ዋነኛው የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ነው።
ጥናቱ እንደሚያሳየው አውሮፓ ራሷ ቡና የማታመርት ብትሆንም እ.ኤ.አ. በ2025 ከቡና ዘርፍ ከግማሽ ትሪሊዮን ዩሮ በላይ የምጣኔ ሀብት ምርታማነት (Economic Output) እና 251.5 ቢሊዮን ዩሮ አጠቃላይ የተጨመረ እሴት (GVA) አግኝታለች።
እ.ኤ.አ. በ2025 ብቻ ወደ አውሮፓ 18.7 ቢሊዮን ዩሮ የሚያወጣ 2.9 ሚሊዮን ቶን ቡና የገባ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ከ97 በመቶ በላይ የሚሆነው አምራች ሀገራት የላኩት ያልተቆላና ያልተቀነባበረ አረንጓዴ ቡና መሆኑ ተጠቅሷል።
ሰነዱ እንደሚጠቁመው ቡናን የመቁላትና የማቀነባበር ሥራዎች የሚከናወኑት ምርቱ ከሚመነጭባቸው አገሮች ይልቅ ወደ ሸማቹ ማኅበረሰብ በቀረቡ የአውሮፓ ቀጣናዎች ነው።
እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አምራች ሀገራት ያልተቆላና እሴት ያልተጨመረበት አረንጓዴ ቡና ብቻ በብዛት የሚልኩ ሲሆን አውሮፓውያን ግን ቡናውን ካስገቡ በኋላ በማከማቸት፣ በመቁላት፣ ካፌይን በመቀነስ፣ ፈጣን (Soluble) ቡና በማምረት እና በተለያዩ የችርቻሮ ሽያጭ፣ የሆቴልና ቱሪዝም (Hospitality) ዘርፎች ላይ በማዋል ከፍተኛውን ጥቅም ለራሳቸው ያተርፋሉ።
የጥናቱ የምጣኔ ሀብት ማባዣ (Economic Multiplier) ሙሉ ሐሳብ እንደሚያሳየው፤ እያንዳንዱ አምራች ሀገር 1 ዩሮ የሚያወጣ አረንጓዴ የቡና ምርት ወደ አውሮፓ ገበያ ሲያስገባ፣ ቡናው አውሮፓ ከገባ በኋላ በሚደረግለት ፦
- የማቀነባበር፣
- የማሸግ፣
- የችርቻሮ ሽያጭ እና በካፌዎች አማካኝነት በሚቀርብበት ሰንሰለት ውስጥ አልፎ 11.20 ዩሮ ቀጥተኛ የአውሮፓ ምጣኔ ሀብት ምርታማነትን (Direct European Economic Output) ይፈጥራል።
ይህ መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ መወሰዱን እንገልጻለን።
@tikvahethiopia