ፕሪሚየር ኮሌጅ በበየነ መረብ (ኦንላይን) ያስተማራቸውን 92 የማስተርስ ተማሪዎችን አስመረቀ።
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

ፕሪሚየር ኮሌጅ በበየነ መረብ (ኦንላይን) ያስተማራቸውን 92 የማስተርስ ተማሪዎችን አስመረቀ።
ፕሪሚየር ኮሌጅ ከኢፌዴሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ሙሉ ዕውቅና ባገኘባቸው ሶስት የትምህርት ዘርፎች በበይነ-መረብ ያሰለጠናቸውን 92 የማስተርስ ተማሪዎች አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ 31 በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ፣ 48 በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና 13 በሊደርሺፕ የማስተርስ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።
የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አህመድ ፈንታው በምረቃው ላይ ተማሪዎቹ በስራ፣ በቤተሰብ ኃላፊነትና በትምህርት መካከል ሚዛን በመጠበቅ በርካታ ፈተናዎችን አልፈው ለዚህ ውጤት መብቃታቸውን ገልጸዋል።
በተለይ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እየሰሩ የሚማሩና ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚከታተሉ በመሆናቸው የኢንተርኔት መቆራረጥና የመብራት መጥፋት ተግዳሮቶች እንደነበሩ ገልጸዋል። ሆኖም ኮሌጁ የመምህራንን የድምፅና የቪዲዮ ትምህርቶች በሲስተሙ ላይ በመመዝገብ ተማሪዎች በሚመቻቸው ጊዜ እንዲከታተሉ ማስቻሉን ጠቁመዋል።
የዋንጫ ተሸላሚው ተመራቂ ተስፋጽዮን ገ/ዮሃንስ በበኩሉ፣ " ይህን ውጤት ለማስመዝገብ ቁርጠኝነት ይጠይቃል፤ ሥራንና ትምህርትን ማጣጣም፣ የቤተሰብና የልጆች ኃላፊነትን መወጣት ተግዳሮት ነበር " ብሏል። በትምህርቱ 4.0 ነጥብ እና 11 A+ በማምጣት የኮሌጁ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ኮሌጁ በቀጣይ በጄኔራል ፐብሊክ ሄልዝ እና ዳታ ሳይንስ የማስተርስ ፕሮግራሞችን ለመክፈት እየሰራ ሲሆን፣ ከታወቁ የውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የፒኤችዲ ፕሮግራም ለመጀመርም ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።
ፕሪሚየር ኮሌጅ
@tikvahethiopia