" በድርቁ ምክንያት በደረሰባቸው ከፍተኛ የኑሮ ጫና እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሰባት ወንዶች በአንድ ቀን መርዝ ጠጥተው ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ አድርገው የሁለቱ ህይወት አልፏል " - ጃን…
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" በድርቁ ምክንያት በደረሰባቸው ከፍተኛ የኑሮ ጫና እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሰባት ወንዶች በአንድ ቀን መርዝ ጠጥተው ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ አድርገው የሁለቱ ህይወት አልፏል " - ጃን አሞራ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት
• ከ4 ሺህ በላይ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ለምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።
• ከ3 ሺህ በላይ እንስሳት በመኖ እና በውሃ እጥረት ምክንያት ሞተዋል።
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
በሰሜን ጎንደር ዞን በጃና ሞራ ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ መጠነ ሰፊ ሰብአዊ ቀውስ እያስከተለ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በወረዳው ስር ከሚገኙ 38 ቀበሌዎች መካከል 18ቱ በድርቅ የተጎዱ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች ለከፋ የምግብ እና የውሃ እጥረት መጋለጣቸውን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሷሊህ ሃሰን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
በአካባቢው የተከሰተው የዝናብ እጥረት ለችግሩ ዋነኛ መንስኤ መሆኑን ሃላፊው አመልክተዋል።
በአካባቢው በተለምዶ በግንቦት ወር መጀመር የነበረበት ዝናብ እስከ ሃምሌ 19 ቀን ድረስ በመዘግየቱ አርሶ አደሩ ሰብሉን በወቅቱ ለመዝራት አልቻለም።
በወረዳው ካሉ አጠቃላይ 38 ቀበሌዎች ውስጥ 5ቱ ለመጀመርያ ጊዜ ዝናብ ያገኙት ሐምሌ 19 ቀን ሲሆን ክረምት ከገባ 4 ቀን ብቻ ዝናብ ያገኙ 5 ቀበሌዎችም ስለመኖራቸው ጠቁመዋል።
ከተዘራው 25 ሺ ሄክታር በላይ መሬት ውስጥም ከ8 ሺህ 1 መቶ ሄክታር በላይ የሚሆነው ጭራሽ ሳይበቅል የቀረ ሲሆን፣ በተለይም የጤፍ ሰብል ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ መውደሙን ታውቋል ይህም በአካባቢው ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እክል መፍጠሩ ተገልጿል።
ተዘርቶ ከበቀለው ሰብልም 4 ሺ ሄክታር የሚሆነው የጠወለገ ነው ያሉ ሲሆን በአጠቃላይ ወረዳው ካለው 26 ሺ 659 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ የበቀለው 12 ሺ 126 ሄክታር የሚሆነው ማሳ የተጎዳ መሆኑን እና ምናልባት ለዘር እና ለመኖ ካልሆነ በቀር ለምግብነት በማይሆን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
ይህ የድርቅ አደጋ በሰው ህይወትና በስነ-ልቦና ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንም አቶ ሷሊህ ነግረውናል።
በወረዳው ከሚገኙ ቀበሌዎች አንዱ በሆነው በዋሰል ቀበሌ ውስጥ በድርቁ ምክንያት በደረሰባቸው ከፍተኛ የኑሮ ጫና እና የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሰባት ወንዶች በአንድ ቀን ውስጥ መርዝ ጠጥተው ራሳቸውን ለማጥፋት ሙከራ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ከእነዚህም መካከል የሁለቱ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፣ አምስቱ በህክምና እርዳታ መተርፋቸውን የጽ/ቤቱ ሃላፊ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ከምግብ እጥረት ጋር ተያይዞም በአሁኑ ወቅት 71 ህጻናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ 5029 ህጻናት ደግሞ በመካከለኛ ደረጃ የምግብ እጥረት ላይ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ከ4 ሺህ በላይ ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ለተመሳሳይ ችግር ተጋልጠዋል።
የወንዞች ፍሰት ከ90 በመቶ በላይ በመቀነሱ፣ ህዝቡ ቆሻሻ ውሃ ለመጠጣት ተገዷል። በዚህም ምክንያት እንደ እከክ፣ ወባ እና የደም ተቅማጥ ያሉ ተላላፊ በሽታዎች በወረዳው በስፋት እየተከሰቱ መሆኑ ተመላክቷል።
እስካሁን ባለው መረጃ ከ3 ሺህ በላይ እንስሳት በመኖ እና በውሃ እጥረት ምክንያት የሞቱ ሲሆን፣ ቁጥራቸው ወደ 4 ሺህ የሚጠጉ እንስሳት ደግሞ የተሻለ ሳርና ውሃ ፍለጋ ወደ ጎረቤት አካባቢዎች ተሰደዋል።
በተጨማሪም የአባ ሰንጋ (Anthrax) በሽታ በአካባቢው መከሰቱ የታወቀ ቢሆንም፣ ወረዳው ላይ ምንም አይነት የመድሃኒት ክምችት ባለመኖሩ እና በክልል ደረጃም መድሃኒት ጠፍቶ በገንዘብ ለመግዛት ባለመቻሉ የእንስሳቱ እልቂት ሊባባስ እንደሚችል ስጋት ተፈጥሯል።
እስካሁን ድረስ የመንግስትም ሆነ የሌሎች ተራድኦ ድርጅቶች ድጋፍ በቂ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ሷሊህ፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በሁለት ቀበሌዎች ላይ ጥናት መጀመሩን ጠቅሰዋል።
ይሁን እንጂ ችግሩ ካለው ስፋትና ጥልቀት አንጻር አፋጣኝ የምግብ፣ የመድሃኒት እና የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ካልተመቻቸ ሁኔታው ወደማይመለስ ጥፋት ሊያመራ እንደሚችል በማሳሰብ፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia