ወደ ይዘቱ ዝለል
ቀጥታ ዝማኔ
ሀሁኒውስ

ግልጽና የታመነ ዜና

" ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር " - ሮዛ

ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia

·

አጋራXFacebookTelegramLinkedIn
" ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር " - ሮዛ
" ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር " - ሮዛ

ባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቆ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ጉድ አሰኝቷል።

ቪዲዮው እውነተኛ ነው ? እውነተኛ አይደለም፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ (AI) የተቀናበረ ሐሰት ነው ? የሚሉ ክርክሮችም ተነስተዋል።

በኋላ ላይ ግን " እኔ ተበዳይ ነኝ " ያለች ግለሰብ ወደ ሚዲያ ወጥታ ቪዲዮው እውነተኛ መሆኑን አፍረጥርጣ መስክራለች።

" ተበዳይ ነኝ " ያለችው ስሟ ሮዛ እንደሚባል፣ የአክሱም ነዋሪ እንደሆነችና በከተማው በሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በአስተናጋጅነት እንደምታገለግል ተናግራለች።

ሮዛ " ሱርያል " ለተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በድምፅ በሰጠችው ማብራሪያ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የ " ትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ አረጋዊ " በሥራ ቦታዋ መጥተው ባገኙት የመስተንግዶ እርካታ መነሻ እንደተዋወቋት ገልጻለች።

ከዚያም የሮዛና የጳጳሱ መቀራረብ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ በኋላ ላይ ራሷን እስከ መጥላት ወደ አደረሰ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተበዳይ ነኝ ባይዋ በጸጸት ተናግራለች።

ሮዛ እንደምትለው፣ ጳጳሱ በተደጋጋሚ ጊዜ " ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት " ይህንን መግቻ እንዲሆን ለጳጳሳት መኖሪያ ወደ ተፈቀደ ቤታቸው በመሄድ ጾታዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ቪዲዮ በድብቅ መቅረጿን ተናግራለች።

የቀረጸችውን የቪዲዮ ማስረጃ ወደ ጳጳሱ ልካ ግንኙነታቸው እንዲቆም ብትማጸንም እንዳልተሳካ ተናገራለች።

በድብቅ የቀረጸችውን ቪዲዮ እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላትም ገልጻለች።

ሆኖም ብር ከመቀበል በላይ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህ መሰል ጸያፍ ተግባር ከሚፈጽሙ የሃይማኖት አባቶች እንድትላቀቅ ባሳየችው አቋም፣ እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባት አብራርታለች።

በዚህ ሁኔታ የቀረጸችው ቪዲዮ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ሊለቀቅ ችሏል። ይግም ፍርሃትና ስጋት እንደፈጠረባትም አልደበቀችም።

ሮዛ፣ “ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፍ ሕግ በጽኑ በሚገዙ የሃይማኖት አባቶች መመራት አለባት” ስትል በአጽንኦት አሳስባለች።

በተጨማሪም በአክሱምና ከአክሱም ውጪ እሷን ጨምሮ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።

ከዚህ ቀደም ጳጳሱ ለጵጵስና በታጩበት ጊዜ " ወልደዋል " ተብሎ በቪዲዮ የተደገፈ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭቶባቸው የነበረ ሲሆን የሰጡት መልስ አልነበረም።

በአሁኑ የቪድዮ ጉዳይም ፣ እንዲሁም ሮዛ ላወረበችው የጾታዊ ጥቃት ክስ እስካሁን በይፋ የሰጡት መልስ የለም።

" በደል ደርሶብኛል " ባይዋ ሮዛ በአሁኑ ሰዓት በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ እንደምትገኝ ገልጻለች።

መቀመጫቸው አክሱም የሆኑት አቡነ አረጋዊ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ አይታወቅም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia

ተዛማጅ ታሪኮች