" ትናንት ማታ ወደ 17 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 ሰዎች በላይ ታግተው ተወስደዋል። ይህ የሆነው ዋልጋ አካባቢ ነው " - ጉዳዩን ያጣሩ አካል
ምንጭ፦ TIKVAH Ethiopia
·

" ትናንት ማታ ወደ 17 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 ሰዎች በላይ ታግተው ተወስደዋል። ይህ የሆነው ዋልጋ አካባቢ ነው " - ጉዳዩን ያጣሩ አካል
ተደጋጋሚ የግድያና ጥቃት በሚያስተናግደው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በታጣቂዎች በተፈጸመ አዲስ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና መታገታቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የዞኑ ፖሊስ አመራር እና የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮም ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጧል።
አንድ ጉዳዩን ያጣሩ ታማኝ የመረጃ ምንጫችን በሰጡን ቃል፣ " ትናንት ማታ ወደ 17 ሰዎች ተገድለዋል። ከ10 ሰዎች በላይ ታግተው ተወስደዋል። ይህ የሆነው ዋልጋ አካባቢ ነው " ሲሉ ነግረውናል።
እኚሁ አካል " ጥቃቱ በተለይ ክረምቱ ከገባ ጊዜ ጀምሮ በጣም ተባብሷል " ብለው፣ " ሌላ ጊዜ ታጣቂዎቹ ሁለት፣ ሦስት ሰዎች አግተው ይወስዳሉ፤ አንድ፣ ሁለት ሰው ይገደላል፤ የትናንቱ አይነት ጥቃት ግን ከበድ ያለ ነው " ብለውታል።
አካባቢው ለጥቃት የተጋለጠ መሆኑን አስረድተው፣ " የታጠቁ ቡድኖች አሉ፤ ይመጣሉ፤ መጀመሪያ የፈለጉትን ይገድላሉ። አንዳንዱን ደግሞ አግተው ይወስዳሉ። ጥቃቱ በሳምንት አንድ ቀን የማይኖርበት ጊዜ የለም። አሁን ሰው ከአካባቢው መፈናቀል ጀምሯል " ሲሉ አክለዋል።
በዞኑ ጥቃቱ መደጋገሙን አስታውሰው " እስካሁን ባለን መረጃ ለታጋቾች ማስለቀቂያ ከ34 ሚሊዮን ብር በላይ ተከፍሏል፤ ከ34 ሚሊየን ብር በላይ እንደተከፈለ የተረጋገጠ መረጃ አለን። ይህ አንድ ወር በፊት ያለ መረጃ ነው " በማለትም ተናግረዋል።
በማህበራዊ ሚዲያው እየተሰራጩ ያሉ መረጃዎች፣ " አንድ ብሔር ብቻ እንደተገደለ " ያመለከቱ ሲሆን፣ ዛሬ የአካባቢው ነዋሪ ቀብር ላይ እንደነበር የነገሩን እኚህ መረጃ አቀባያችን ግን " ሟቾች ከሁሉም ብሔር የተሰባጠሩ መሆናቸውን የሚመለከት መረጃ " እንደደረሳቸው ነግረውናል።
በተያያዘ፣ ከአካቢው የወጡ መረጃዎች፣ "ዋልጋ" ላይ ትናንት ጥቃት መፈጸሙን በመጠቆም፣ የሟቾቹ ቁጥር 20፣ የታጋቾች 16 እንደሚደርስ ያመለከቱ ሲሆን፣ በመንግስት በኩል ግን እስካሁን ስለቁጥራዊ መረጃ የተባለ ነገር የለም።
የጉራጌ ዞን ፖሊስ ምን አለ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ትናንት አበሽጌ ወረዳ ላይ ደርሷል ስለተባለው ጥቃት የጉራጌ ዞን ፖሊስን ጠይቋል።
አንድ የፖሊስ አመራር " መረጃው የሚገኘው አካባቢውን በሚመራው ኮማንድ ፖስት ነው፤ ይህም በክልሉ ሰላምና ጸጥታ በኩል ነው የሚመራው። እኛ መረጃ መስጠት አንችልም " ብለዋል።
" በተናጠል ማብራሪያ መስጠት አንችልም፤ የሚመራው በኮማንድ ፖስት ነው " ያሉን እኚሁ አመራር፣ " ጥቃቶች ተፈጽመዋል፤ አደጋ ደርሷል። ማህበረሰቡ የተለያዬ እሳቤ ስለሚይዝ በተጠናጠል የሚብራራ አይደለም " ሲሉ ነግረውናል።
👉 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ወደ አበሽጌ ወረዳ አስተዳደር ሙከራ ቢያደርግም፣ የስልክም ሆነ የፅሑፍ ምላሽ ማግኘት አልተቻለም። ሆኖም ግን ክልሉን ምላሽ ጠይቀናል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሰ ?
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮን ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፣ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጠው ለጥቃቱ " ራሱን 'ፋኖ ነኝ' ብሎ ሰይሞ የሚንቀሳቀስ " ታጣቂ ቡድን አለ በማለት ተጠያቂ አድርገዋል።
ኃላፊው ፦
" እዛ አካባቢ አንድ ገዳይና ዘራፊ ቡድን አለ፤ ራሱን 'ፋኖ ነኝ' ብሎ ሰይሞ የሚንቀሳቀስ ኃይል አለ። ያ ኃይል አሳቻ ሰዓት እየተጠቀመ ንጹሐን ዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው። ጉዳቱንም የሚያደርሰው ብሔር እየመረጠ ነው።
ትናንትም የተወሰኑ ንጹሐን ዜጎች ላይ ጉዳት አድርሷል። ይህን ለመመከት የመንግስት የጸጥታ አካላት በዙሪያው አሉ፤ ያልጠበቀ አሳቻ መንገድ ተጠቅሞ ነው ይህንን ጉዳት በጣም በአጭር እና በጥቂት ደቂቃዎች ላይ ያደረሰው።
የመንግስት የጸጥታ ኃይል ሰላም ለማስፈን የሚያስችል እርምጃ ለመውሰድ በአካባቢው እየንቀሳቀሰ ነው ያለው። እንግዲህ በእነዚህ አካላት ነው የቤት ውድመትም፤ በዜጎች ላይ ጥቃትም እየደር ያለው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ " 'የፋኖ' ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱት አማራ ክልል ነው፤ ማዕከላዊ አትዮጵያ ክልል ላይ እንዴት ሊኖሩ ቻሉ? " የሚል ጥያቄ አዘል አስተያየት የሚያቀርቡ አሉ፤ ለዚህ የእርስዎ ማብራሪያ ምንድን ነው ? ሲል ቢሮ ኃላፊውን ጠይቋቸዋል።
አቶ ተመስገን በምላሻቸው፣ " ራሳቸው (ታጣቂዎቹ) ከሚሰጡት ስያሜ ተስተን ነው እኛ መረጃ የምንሰጠው፤ 'ፋኖ ነን' ነው የሚሉት። 'ፋኖ ነን' ብለው በሚዲያም ይወጣሉ። ኢንፎርማሊ ህዝቡ ውስጥም 'የፋኖ ሴል ነን' ይላሉ" ሲሉ ተናግረዋል።
(ተጨማሪ አለን)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia